የፍርድ ቤት ውሎ!
11 የአማራ ተወላጅ የህሊና እስረኞች በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ቅጣት ቤት በመግባታቸው ለአደጋ መጋለጣቸውን ለልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ፀረ _ሽብርና ህገ መንግስት ችሎት አርቲስት ዮርዳኖስ አለሜ በምሬት አቤቱታ አቀረበ።
በችሎቱ ላይ በምሬት አቤቱታውን ያቀረበው አርቲስት ዮርዳኖስ አለሜ እንዳለው ከሆነ የቃሊቲ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት ወደ አባ ሳሙኤል በመዛወሩ ምክንያት 40 የአማራ ተወላጅ የህሊና እስረኞችን ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ማዕከል መዛወራቸው ይታወቃል።
ይሁን እንጂ 11 የህሊና እስረኞችን በመነጠል በተለምዶ ቅጣት ቤት ተብሎ የሚጠራው ማለትም በተለያየ ችግር ምክንያት የስነ ምግባር ችግር ያለባቸው እና በኦነግ ሽኔ የሽብር ቡድን ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ የነበራቸው ነፍሰ ገዳዮች ጋር ሆን ተብሎ እንድንገደል በማቀድ ማረሚያ ቤቱ ሂወታችንን አደጋ ላይ ጥሎታል። እኛም አለ አርቲስቱ በማንኛውም ሰአት ልንሞት (ልንገደል )እንደምንችል በማወቃችን ሌሊት ያለ እንቅልፍ ቁጭ ብለን ለማደር ተገደናል በማለት ለችሎቱ አስረድቷል።
አርቲስቱ ሲቀጥልም በዚህ ችግር ውስጥ የወደቅነው
1ኛ. የተከበሩ ዮሀንስ ቧያለው
2ኛ. እኔ አርቲስት ዮርዳኖስ አለሜ
3ኛ. አቶ አብድሮህማን አህመዲን (የቀድሞ የፓርላማ አባል )
4ኛ. ኢንስፔክተር ፍርዱ ታፈረ
5ኛ. ዋ/ሳጅን ጎረፈ ወጣት
6ኛ. ኢንስፔክተር የሺዋስ አልታሰብ
7ኛ. ዲያቆን ገ/ሚካኤል አባይ
8ኛ. ወጣት አማኑኤል ያለው
9ኛ. አቶ አማኑኤል በለጠ
10ኛ. አቶ ንጉስ ጥላሁን
11ኛ. አቶ ጥላዬ ይታየው ነን፣ ይሁን እንጂ ችሎቱ ምንም እንኳ ፍርድ ቤቶች የሰብአዊ መብቶችን የማክበርና የማስከበር ህገ መንግስታዊ ሀላፊነት ያለባቸው ቢሆንም እንደተለመደው የአማራ ተወላጅ የህሊና እስረኞችን ህይወት አደጋ ላይ መሆን ቸል በማለት ለብልፅግና አስፈፃሚዎች በመወገን በዝምታ አልፎታል ሲል በችሎቱ መናገሩን በችሎቱ የታደሙ የአይን እማኞች ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል።