“ፋኖ መሆን ቀላል ነው” - ብልፅግና!
አዲሱ አረጋ የብልፅግናን የማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊት እያደራጀና እያሰለጠ ነው፡፡ ስልጠናው በተከታታይ እየተሰጠ ይገኛል፡፡ በሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ በሚሰጠው በሁለተኛው ዙር ስልጠና ላይ አዲሱ አረጋ የማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊቱ እንዴት ገዥ ትርክቱን (ገዥ ትርክት የሚሉት በኦሮሙማ አምሳል የትገነባዋን ኢትዮጵያን የሚገልፀውን ትርክት ነው) እንዴት ማስረፅ እንደሚቻል፣ እንዴት የከሸፈውን ትርክት (ነባሩን የኢትዮጵያ ትርክት ማለት ነው) መምታት እንደሚቻል ወዘተ ምሳሌ እያጣቀሰ ያስረዳል፡፡ አዲሱ ከጠቀሳቸው ምሳሌዎች ውስጥ አንዱ ፋኖ እና የፋኖ አስተሳሰብ ነው፡፡ ኦሮሞ ሳይሆን በጉዲፈቻ ኦሮሞ ነኝ ብሎ የሚኖረውና ከጳጳሱ በላይ ካቶሊክ ሊሆን የሚፈልገው አዲሱ አረጋ “ፋኖን በሚመለከት ብዙ የሚፃፍ ነገር አለ፡፡ ለምሳሌ ፋኖ መሆን ቀላል መሆኑን እየገለፃችሁ መፃፍ በራሱ ጃዊሳውን ራቁቱን ያስቀረዋል፡፡ ፋኖ ለመሆን የሚስፈልገው አላማ አይደለም፡፡ ቁርጠኝነትና ህዝባዊነት አይደለም፡፡ ጀግንነት አይደለም፡፡ ፋኖ ለመሆን የሚያስፈልገው አንድ ትልቅ አንገት ላይ የሚንጠለጠል እንጨት መስቀልና አንድ ስናይ ክላሽ ብቻ ነው፡፡ እሱን ይዞ ሰብሰብ ብሎ ፎቶ ተነስቶ የእከሌ ብርጌድ ብሎ መልቀቅ ነው፡፡ ከዚያ የእንትና ጉማጅ፣ የእከሌ ግልገል እየተባልክ ስም ይሰጥሃል፡፡” እያለ ሲቀደድ ከርሟል፡፡
አዲሱ ጠላት በመሆኑ ከዚህም የከፋ ነገር ይናገራል፡፡ ከዚህም የከፋ ያደርጋል፡፡ የአብይ አገዛዝ ምን ያህል የፋኖን ስም ለማጠልሸት ዝግጅት እያደረገም የሚያሳይ ነው፡፡ ሆኖም ይህ ሁሉ ከጠላት የሚጠበቅ ነው፡፡
የጠላት ስም ማጥፋትና ማጠልሸት እንደተጠበቀ ሆኖ እኛስ ለጠላት ምሳር የሚያቀብል ስራ አንሰራም ወይ ብለን ራሳችን መጠየቅ አለብን፡፡ ቤትን መፅዳት ወሳኝ ነው፡፡ የኃይማኖት ጉዳይ እጅግ ሲበዛ ስስና ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ነው፡፡ የአማራ ብሄርተኝነት ፍፁም ሴኩላር የሆነ ሁሉም ሃይማኖቶች በነፃነት የሚኖሩበትን ሁኔታ ለመፍጠር የሚታገል እንጅ ራሱን ከአንድ ወይም ከሌላ ኃይማኖት ጋር ማጣበቅ አይቻለውም፡፡ እንዲህ ማድረግ ለብሄርተኝነታችንም ለኃይማኖት ተቋማትም አይጠቅምም፡፤ ሁሉም በየፈርጁ መቀመጥ አለበት፡፡
በተመሳሳይ መልኩ የህዝብ ግንኙነትና ፕሮፓጋንዳ ስራም ራሱን የቻለ ጥበብ ነው፡፡ የፋኖ አርበኞች በስሜት ሳይሆን በከፍተኛ ዲሲፕሊንና ድርጅታዊ አሰራር መማራት አለባቸው፡፡ በስነ ምግባራቸውና በህዝባዊነታቸው የተመሰረከረላቸው መሆን አለባቸው፡፡ እንኳን እነሱ በሌብነትነ በስርቆት ሊሰማሩ በሌብነትና ዘረፋ የተሰማሩትንም መቅጣት አለባቸው፡፡ ራሳቸውን ከሽፍታና የጦር አበጋዝ ስነ ልቦና ማራቅ አለባቸው፡፡ ለሚዲያ ቃለ ምልልስ መስጠት ያለበት አካል እና ያ አካል በየስንት ጊዜው ቃለ ምልልስ እንደሚሰጥ የተቀመጠ አሰራር ያስፈልጋል፡፡ ሌሎቻችንም ከተማ ቁጭ ብለን እየደወልን መረጃ የምንጠይቅ መታረም አለብን፡፡
አሁን ከሚታዩትና በፍጥነት መታረም ካለባቸው ችግሮች አንዱ ስልክ አጠቃቀም ጉዳይ ነው፡፡ ስልክ መያዝ ያለባቸው እጅግ የተመረጡ ውስን ሰዎች እንጅ ሁሉም ታጋይ ስልክ ይዞ የሚታገል ከሆነ አደጋ ነው፡፡ በሙሉ ልቡ ሊታገል አይችልም፡፡ የድሮን ሲሳይ ከመሆንም አያመልጥም፡፡