ጥር 09/2017 ዓ.ም
በወቅታዊ ጉዳይ ከጉና ክ/ጦር የተሰጠ መግለጫ///
የኅልውና ትግላችንን ከጠንጋራ አስተሳሰብ አራማጆች የመጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነት አለብን!!!
አማራን በማንነቱ ምክንያት በጠላትነት ፈርጆ የተነሳው የብልጽግና ሥርዓት የሥልጣን መደላድሉን፣ የሃገረ መንግሥት ሥሪቱን ያደላደለው በጸረ አማራነት አስተሳሰብ ላይ የተዋቀረ ሕዝብን በጠላትነት ፈርጆ የዘር ማጥፋት ግብሩን በመንግሥታዊ መዋቅር እያስፈጸመ የሚገኝ ሥርዓት ነው። የክፉም የመልካምም ሥራ መቅድሙ አስተሳሰብ ነው። አማራን እንደሕዝብ የዘር ማጥፋት ድርጊት እየፈጸመ የሚገኘው ሥርዓት አስተሳሰቡ ትናንት በነጻ አውጭነት ስም ጫካ ውስጥ የተጸነሰ አጋጣሚውን ሲያገኝ በሥልጣን የተወለደ፣ በመንግሥት መዋቅር አድጎ ስሁት አስተሳሰቡን ጠላት በሚለው የአማራ ሕዝብ ላይ በገሐድ እየፈጸመ ያለ ስለመሆኑ የአደባባይ ሐቅ ነው።
አማራው ኅልውናው እንዳይጠፋ፣ ሰብዓዊ ክብሩ እንዲረጋገጥ፣ ነጻነትና እኩልነቱ እንዲረጋገጥ ታላሚ ባደረገ ሐቀኛ የኅልውና ትግላችን ውስጥ የበቀሉ የትግላችን ሾተላይ አስተሳሰቦች ከመጸነስ አልፈው ከትግል ዓላማችን በተጻራሪ መንገድ በገቢርም ጭምር እያየናቸው እንገኛለን። ከሕዝባችን ፍላጎት በተቃራኒ፣ ከግብና ዓላማችን ባፈነገጠ መልኩ ይልቁንም የሥርዓቱ መጠቀሚያ በሚሆን መልኩ ፍላጎቱን፣ ደስታውን፣ ሕይወቱን ለአማራ ሕዝብ ገብሮ ጫካ የሚገኘውን የኅልውና ታጋይ አንድነትና መስተጋብር የሚንዱ ተግባራት እጅ እግር አውጥተው ክፍለ ጦራችንን እና ትግላችንን ከትናንት እስከ ዛሬ እየፈተኑ ይገኛሉ። በትግል ሜዳ የግል ፍላጎት ቦታ የለውም፤ በትግል ሜዳ መለያዬት የግጭትና የመጠፋፋት መንገድ መሆን የለበትም፤ በትግል ሜዳ አደረጃጀቶችን በተሳሳተ መንገድ ለግል የፖለቲካ ፍጆታ መጠቀሚያነት ማፍረስ ጸረ አማራነት እንጅ የኅልውና ትግላችን ካንሰር ነው።
እንዲህ ያሉ አስተሳሰቦች የወለዷቸው ችግሮችን ለመግራትና ለማረም ጊዜ ወስደን መክረናል፤ ትግላችን ላይ ብቻ እንድናተኩርም አቅጣጫዎችን ሰጥተናል። በተለይ ደግሞ የጉና ክፍለ ጦር በሚንቀሳቀስባቸው ቀጠናዎች የፋይናንስ ተቋማትን የመዝረፍ፣ ግብራቸው የጠላት ግን የፋኖን ጭንብል በለበሱ የኅልውና ትግላችን ነቀርሳዎች ማኅበረሰብን በማሳቀቅ ፋኖን ከሕዝብ የመነጠል ልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎች የተከናወኑ ሲሆን በክፍለ ጦራችን ልዩ ኦፕሬሽን እየተሠራ መፍትሄ ስናበጅ መቆየታችንም ይታወቃል።
ጉና ክፍለ ጦር የተቋማችን የአማራ ፋኖ በጎንደርን ተቋማዊ አሠራር አክብሮ የሚንቀሳቀስ በቀጠናው ከሚገኙ አደረጃጀቶች ጋር ተቀናጅቶ ጠላትን ቅስም የሚሰብር የጽኑ ጀግኖች አደረጃጀት፣ ከምንም በላይ ትግላችን በጀግንነት የተሰውትን አደራ ለደቂቃም ሳይዘነጋ በየእለቱ አደረጃጀቱን እያሰፋ የጠላት መጋኛ መሆኑ በውል እየታወቀ አደረጃጀታችንን ለማፍረስ እንቅልፍ አልባ ሰይጣናዊ ቀናተኞች አሁንም አርፈው አልተቀመጡልንም። እነዚህ አካላት ባለማወቅ ቢሆን ትናንት ተመክረው እንዲመለሱ ሲደረጉ እንዲህ ባለ እኩይ ግብራቸው ባልቀጠሉ ነበር፤ ከቀጠናችን አንድም ከአደረጃጀታችን ከምንም በላይ ከትግል ሐቀኛ እሳቤያችን አፈንግጠው ከላይ የዘረዘርናቸውን አስነዋሪ ድርጊቶችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልኩ ሲፈጽሙና ሲያስፈጽሙ የነበሩ ባለዲግሪ ደናቁርት ተልዕኮ ሰጭነት በብርቱ እየፈተኑን ቢገኙም ከተቋማችን ከፍተኛ አመራሮች ጋር በወጉ መክረን ነገሮችን ለማስተካከል ሌት ተቀን በመድከም ላይ እንገኛለን። እነዚህ አካላት የጉና ክፍለ ጦር የብርጌድ አደረጃጀት ውስጥ የሚገኙ ሁለት ሻለቃዎችን ወስደው የክፍለ ጦር ስያሜ ሰጥተው ጉና ክፍለጦርን ለማፍረስ የሄዱበት የጥፋት መንገድ ሙሉ በሙሉ በጀግኖቹ ከሽፏል። ድርጊቱ የትናንቱ ፋሕፍዴን፣ ሕዝባዊ ግንባር ጥምረት ወለዱ ሕዝባዊ ድርጅት የሚባል አደረጃጀት አመራሮች ስምሪት የሰጡበት ነውረኛ ተግባር ነው።
ስለሆነም የጉና ክፍለ ጦር አመራሮችን ትናንት ጠላት ሲያሳድዳቸው የኖሩ የጠላት ማርከሻዎችን ዛሬ ደግሞ ራስ ጋይንት፣ ገብርዬ፣ ጄኔራል ነጋ በሚል የክ/ጦር ስያሜ የሚንቀሳቀሱ ወንድም ያልናቸው አካላት በጉና ክ/ጦር ቀጠና አስነዋሪውን የጥፋት ተግባር እየፈጸሙ ይገኛሉ። የድርጊቱ መሪዎችም ከፍያለው ደሴ፣ አዲሱ ደባልቄ፣ ጸዳሉ ደሴ፣ እያሱ አባተ እና ጌታ አስራደ ዋነኞቹ ናቸው። ስለሆነም ይህንን አስነዋሪ ድርጊት የሚዲያ አካላት እንድታወግዙልን እና ለሕዝብ እንድትገልጹልን አደራ እንላለን፤ ከምንም በላይ የክፍለ ጦራችንን የአሥተዳደር ቀጠናም በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ ጥብቅ መልእክታችንን ለማስተላለፍ እንወዳለን።.
ኅልውናችን በተባበረ አንድነታችን!!!
ጉና ክፍለ ጦር