"ሰማይ ተደፍቶብኛል፡ የበሬ ቀምበር እንኳን አልተረፈልኝም" በቤታቸው ፍርስራሽ አመድ ላይ ቁጭ ብለው የሚያለቅሱ አባት!
በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ ድብኮ ቀበሌ ልዩ ስሙ እንኮይበር በተባለ አከባቢ የአገዛዙ ወታደሮች የፋኖ ደጋፊ ናችሁ በሚል መኖሪያ ቤቶችን ቤንዚን አርከፍክፈው በእሳት አቃጥለዋል።
በምስሉ ላይ የምትመለከቷቸው ጎልማሳ አባት በቅርቡ ባለቤታቸውን በሞት የተነጠቁ ሲሆን፡ የባለቤታቸውን አርባ ለማውጣት ዝክር ሲዘክሩ የተመለከቱት የአገዛዙ ወታደሮች "ፋኖን ልታበሉ ነው" በሚል መኖሪያ ቤታቸውን በእሳት አቃጥለውባቸዋል።
ድርጊቱ የተፈፀመው ጥር 09/2017 ዓ/ም እኩለ ቀን ገደማ ነው። ወታደሮቹ ቤቱ በእሳት ተቃጥሎ እስኪጨርስ ማንም ሰው እሳቱን እንዳያጠፋ ቁጭ ብለው ሲከለክሉ እንደነበርም ተነግሯል።
© መረብ ሚዲያ