የአፋብን አሳምነው 5ኛ ዕዝ አፄ ዘርያዓቆብ ፩ ኮር ናደው ክፍለ ጦር አስደናቂ ጀብድ ፈፅሟል !!
ነሐሴ 18/2018 ዓ ም
የአገዛዙ 101ኛ አየር ወለድ ኮማንዶ በሆድ አደሩ ሚሊሻ መንገድ መሪነት በ ቀን 17/12/2018 ዓ.ም መነሻውን ከመርሐቤቴ ፌጥራ ከተማ በማድረግ ፋኖ ይንቀሳቀስበታል ብሎ ወደገመተው ታችቤት ቀጣና ጥቃት ለመፈፀም እየተግተለተለ በሦስት አቅጣጫ የተንቀሳቀሰ ቢሆንም የናደው ክፍለ ጦር የውጊያ ጠበብቶችና ፈጣን ተዋጊዎች ጠላት ያሰበበት ቦታ ሳይደርስ ፈጣን ጥቃት በመፈፀሙ ለቀናት የተሰናዳበት ዕቅድ ከሸፈ።
የጠላትን ዕቅድ ቀድሞ የደረሳቸው የናደው ክፍለ ጦር ቃኝዎች ወደ ፌጥራ ከተማ ልዩ ስሙ ጉራንባ የተባለ ቦታ ላይ የመሸገውን የጠላት ኃይል ላይ ከቀኑ 8:00 ሰአት ላይ ተኩስ በመክፈት አመርቂ ድል ተጎናፅፈዋል። በነበረው አውደ ውጊያ በወገን ኃይል የበላይነት የጠላት ኃይል በርካታ ሙት እና ቁስለኛ ሲሆን የቀረው የጠላት ኃይል በውር ድንብር ለማፈግፈግ ሲሞክር በተኩስ ጫና የገደል ሲሳይ ሆኗል።
በእዚህ የተደናገጠው የጠላት ሀይል ማጥቃት የሚለው የህልም እንጀራ ከሽፎበት ቀሪውን ኃይሉን ለማትረፍ በፍጥነት ኃይል ጨምሮ ወደ አንድ አቅጣጫ ማለትም ወደ ፌጥራ ከተማ ተግተልትሎ በመግባት የተለመደውን የፈሪ ብትሩን በፌጥራ ከተማ ንፁሃን ወጣቶች እና ከተማ ውስጥ በተገኙ አዛውንቶች ላይ በድብደባና በማሰር የማይረባ ድርጊቱን ሲፈፅም አምሽቷል ሲል የግንባር መረጃችን ገልጿል።
በሌላ በኩል ከትናንት በስተያ የናደው ክፍለጦር በቀንደኛ ሁለት ባንዳዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰዱን ገልጿል።የክ/ጦሩ ተንቀሳቃሽ ቃኝዎች ለስራ በተሰማሩበት በመርሐቤቴ ላይቤት ወረዳ ከአለም ከተማ በቅርብ ርቀት በምትገኝ ልዩ ስሟ እራስመስክ ቀበሌ ከቀኑ 9:30 ላይ በመከላከያ ተልዕኮ ሰጭነት የፋኖን እንቅስቃሴ ለስለላ እና ከተሰጣቸው ተልዕኮ ጉን ለጎን የፋኖን ስም ለማስጠልሸት በከተማ ቅርብ ርቀት እየዘረፉ ባሉበት እርምጃው ተወስዷል ተብሏል። በዚህም :-
1) አቶ አባወይ አየለና 2) አቶ አስፈራ ቡችሌ ላይ ኦፕሬሽን በመስራት ህዝባችንን ከዘረፋ የገላገለና የአገዛዙን የስለላ መረብ የመበጠሰ ስራ ተሰርቷል ። በእነዚህ ግለሰቦች ላይ በተበደለው ህዝባችን ጥቆማ በፋኖ ጠንካራ መረጃ ማጣራትና ትብብር እርምጃው የተወሰደ ሲሆን አቶ አባወይ አየለ የተባለው ባንዳ ከዚህ ቀደም የናደው ክፍለ ጦር አባል የነበረ እና መሳሪያ ይዞ ከድቶ ለአገዛዙ ያደረና እና ህዝቡን በመካድ የጠላት መንገድ መሪ ሆኖ ሲያገለግል የነበረ በመሆኑ እና ተደጋጋሚ ምክር የተሰጠው ቢሆንም ከጥፋቱ ባለመታረሙ ከእነ ግብረ አበሩ አቶ አስፈራ ቡችሌ የማያዳግም እርምጃ ተወስዶበታል። ክፍለጦሩም ሌሎች ባንዳና የሚሊሻ አባላት ከዚህ በመማር ከእኩይ ድርጊታችሁ ተቆጥባችሁ ወደመደበኛ ሂይወታችሁ ተመለሱ ያለ ሲሆን፤ ለዘረፋ ሲጠቀሙበት የነበረው የጦር መሳሪያም ወደ ክ/ጦሩ ገቢ ተደርጓል ሲል ኮሩ በላከው መረጃ አክሎ ገልጿል።
ክብር ለትግሉ ሰማዕታት
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አፋብን አሳምነው 5ኛ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ