የፖስፖርት የግዜ ቆይታ ከአምስት ዓመት ወደ አስር ዓመት ከፍ ማለቱ ተገለጸ
የኢሚግሬሽን ዜግነትና አገልግሎት የፖስፖርት የግዜ ቆይታ ከአምስት ዓመት ወደ አስር ዓመት ከፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
ፖስፖርት ለማደስ አምስት ዓመት ይጠበቅ እንደበር የሚታወቅ ሲሆን፤ ከአንድ ወር በኃላ ወደ ሥራ በሚገባዉ አሰራር መሰረት ግን 25 ዓመት ለሟላቸዉ ዜጎች በየ10 ዓመቱ እንደሚታደስ አገልግሎቱ ገልጿል።
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የዋጋ ጭማሪ ካደረጉ ቀዳሚዎቹ የሆነዉ የኢሚግሬሽን ዜግነትና አገልግሎት በፖስፖርት ላይ ጭማሪ ማድረጉ አይዘነጋም።
ተቋሙም ማሻሻያዉን ካደረገ በኃላ በሩብ ዓመት አፈፃፀሙን በተመለከተ በዛሬዉ ዕለት ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል።
በመግጫዉም ለጋዜጠኞች ማብራሪያ የሰጡት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊ ዳዊት በሦስት ወራት ዉስጥ ለ22 ሺሕ ዜጎች አስቸኳይ ፖስፖርት መስጠቱን ተናግረዋል።
ዋና ዳይሬክተሯ ከፖስፖርት ጭማሪ ጋር በተያያዘ ለተነሳላቸዉ ጥያቄ፤ "ዋጋ ጭማሪዉ ከሌሎች ሀገራት ጋር ሲነፃፀር በጣም ትንሹ ክፍያ ነዉ ብለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ 4 መቶ 78 ሺሕ የሚሆኑ ፖስፖርቶች ከዉጭ ማስገባቱ የተገለጸ ሲሆን፤ ለ357 ሺሕ ደንበኞች የማስተላለፍ ሥራ ተሰርቷል ተብሏል።
ከነሐሴ ወር ጀምሮ ለ22ሺህ ዜጎችም አስቸኳይ ፖስፖርት መስጠቱን የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አስታዉቋል።
በተጨማሪም የአቅም ዉስንነትን ከመቅረፍ አኳያ የተሻለ አፈፃፀም ተመዝግቧል ተብሏል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news