በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቤተ-ሙከራዎች ውስጥ የሚገኙት መጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ኬሚካሎች ቆጠራ በመካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ።
በትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት መሪ ሥራ አስፈጽሚ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቤተ-ሙከራዎች ውስጥ የሚገኙት መጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ኬሚካሎች ቆጠራ በመካሄድ ላይ መሆኑ ገልጿል፡፡
የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች ተጠባባቂ መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰራዊት ሃንዲሶ(ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ሥራ ክፍሉ በ2017 ዓ.ም በአቅድ ከያዛቸው የሪፎርም ስራዎች መካከል አንዱ የምርምር ግብዓቶችንና ፋሲሊቲዎችን በማሻሻል የቤተ-ሙከራ ስታንዳርዳይዜሽንን እና አክሬዲቴሽን ስርዓትን መዘርጋት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አክለውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ የኢንዱስትሪ፤ የምርምር እና የላብራቶሪ ኬሚካሎች አያያዝ፤ ክምችትና የማጓጓዝ ሂደትና የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸውን ኬሚካሎች የቆጠራ ሥራ ለመሥራት እንዲቻል ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ይህ ሥራ የሚሰራው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብቻ ሳይሆን በአቅራቢያቸው በሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስር ባሉ ቤተ-ሙከራዎች ውስጥ የሚገኙትን ኬሚካሎች ምንጭ፣ አይነት፣ ደረጃ፣ መጠን እና ባህሪይ የማወቅ መረጃ የማሰባሰብ ሥራ እንደሚሰራም ሃላፊው ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news