እጅግ የበዙ የኃጢአት ልምምዶች ውስጥ ልንሆን እንችላለን። ከዛሬ ነገ እያልን እዛው ጭልጥ ብለን የቀረን ብዙዎች ነን። ወገኖቼ፣ ተስፋ አለ! ዳዊትን ያገኘው ምሕረት እነሆ እኛንም ሊያገኘን ይናፍቃል። ምንም እንኳን ተስፋ በሚያስቆርጥ ሁኔታ ውስጥ ብንሆን ተስፋ አንቁረጥ። ሰማይንና ምድርን በቃሉ ያበጀው አምላክ በከብቶች በረት ሰው ሆኖ የተወለደው ለአንተ፣ ለአንቺ፣ ለእኛ ነው። በደላችንን በመስቀል ላይ የተሸከመው እኛ ነፃ እንወጣ ዘንድ ነው። በእርግጥ መለወጥ ይቻላል። በእግዚአብሔር ዘንድ የተገለጠው ይህ አስደናቂ ምሕረት አስደናቂ የሆነን ለውጥ በሕይወታችን ያመጣል። አዎን፣ “ምሕረትህ ከሕይወት ይሻላልና ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።” (መዝ 63፥3)
FOLLOWING THE KING
ንጉሱን መከተል
KNOW I OBEY I REST
ማወቅ I መታዘዝ I ማረፍ
Follow Us On INSTAGRAM YOUTUBE
FOLLOWING THE KING
ንጉሱን መከተል
KNOW I OBEY I REST
ማወቅ I መታዘዝ I ማረፍ
Follow Us On INSTAGRAM YOUTUBE