እግዚአብሔር ባለ መድኃኒት አድርጎ ለህዝቡ የመረጣቸው እድለኞች እንደ መንደር ጎረምሳ ሸክም ሲሆኑበት ፤ የህዝቡን ጭንቀት እንዲያቀሉ የተጠሩ ይባስ ቀንበርን ሲያከብዱባቸው፤ በፍርሃት ውስጥ ላሉ የተስፋን ጭላንጭል፣ የእግዜሩ ድምፅ ማሳያ ሊሆኑለት ሲያቅታቸው፤ መድሃንያለም አንዱን ልጁን መድኃኒት አድርጎ ለሰው ልጅ ሁሉ ሰጠው!
ይሄ የተወለደው ንጉስ መድኃኒት እና ብርሃን ነው። በክፉ ትዕቢታችን ለታሰርንበት የሀጥያት፤የሰይጣን እና የሞት እስራት ብቸኛ መፍትሔ ሆኖ መጥቶልናልና!
ከጨለማ ሊያወጣን የሚያበራ የንጋት ኮኮብ ሆኖ ፤የተቀባው መሲህ ሰላምን ይዞ መጣልን!
በነፍሳችን ሁካታ ስንኖር ለነበርን አመፀኛ እና ተስፋ ቢስ ተቅበዝባዦች የእረፍት ስጦታ ይዞ ፤ ለህዝቦች ሁሉ የሚሆነው የአለም መድኃኒት ሊጎበኘን መጣ፤ ጌታ ኢየሱስ መጣ!
ሉቃስ 2፥10
እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።
መልካም የልደት መታሰቢያ በዓል
Amanuel.T
FOLLOWING THE KING
ንጉሱን መከተል
KNOW I OBEY I REST
ማወቅ I መታዘዝ I ማረፍ