♡ ልቤ ያውቀዋል ♡
ልቤ ያውቀዋል ያደረክልኝ ነገር
የሰራህልኝን ስራ
መድኃኔዓለም አወጣህኝ ከመከራ
በቃል ጉልበት አይወራ (2)
አዝ
መስቀል ተሸክመህ በደም ርሰህ
እኔን በመከራ ዳግም ወልደህ
በክብር ተሻገርኩ ክሰህልኝ
በህይወት አቆምከኝ ወድቀህልኝ
አዝ
የበደሌን ጋራ አቀበቱን
የባርነት ሰነድ እዳ ክሱን
አጥፍተህው ጌታ መድሀን ሆነ
እርቃኔ በእርቃንህ ተሸፈነ
አዝ
በፍቅርህ መአዛ እርክቷል ልቤ
በማይቆም መውደድህ ተከብቤ
የህይወቴ ወደብ መስቀልህ ነው
ወጀብ እና ንፍስ የማይነቅለው (2)
አዝ
የእሾህ አክሊል ደፍተህ ኤልሻዳይ
እፎይ አለ ልቤ ከስቃይ
ሆኖልኛል መዳን አንተ ተማህ
ነፃ ወጣሁ ሸክሜን አንተ ተሸክመህ
አዝ
ዙፍንህን አስተወህ የኔ ፍቅር
ከሰማይ ሀገርህ መጣ በምድር
ታየህ ስትፈልገኝ ልጄ ብለህ
ፈራጅና አስዳቂ አምላኬ ነህ (2)
መዝሙር
ሊቀ ዲያቆን ዘማሪ ነብዮ ሳሙኤል
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@yetewahedofera
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈