🌍💫በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲቲዩት የሳይኮሜትሪክ ምዘናን መሠረት ያደረገ ምደባ!
በሥራና ክህሎት ሚኒስትር በለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት E-LMIS የሳይኮሜትሪክ ምዘና ሰልጣኞች ውስጣቸው ያለውን ተሰጥኦ፣ ዝንባሌና ልዩ ችሎታ በመረዳት የሥልጠና ዘርፋቸውን መለየት የሚችሉበት አገልግሎት ነው።
በዚህም መሠረት በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲቲዩት ለሚገኙ 212 ሰልጣኞች ካላቸው የትምህርት ውጤት በተጨማሪ የሳይኮሜትሪክ ምዘና በመስጠት እንደየ ተሰጥኦዋቸው፣ ዝንባሌና ልዩ ችሎታቸው እየታየ ምደባ ለማከናወን ወደ ሥራ የተገባ ሲሆን ይህ ስርዓት ሰልጣኞች በስልጠና ላይ እና ከስልጠና በኋላ በሥራው ዓለም ሲሰማሩ ስኬታማ መሆን የሚችሉበትን አቅም የሚፈጥር ነው። በተጨማሪም በቀጣይ ተደራጅተው ለመስራት የብድር አገልግሎት ቢያስፈልጋቸው የሳይኮሜትሪክ ምዘና ውጤታቸው ለብድር አገልግሎት እንደ አንድ መመዘኛ ማቅረብ የሚችሉበት ትልቅ አገልግሎት ነው።
እንደ ሃገር ሰልጣኞች ሊሰሩበት እና ስኬታማ ሊሆኑበት በሚችሉት የሞያ ዘርፍ መመደባቸው ያለውን የሰው ሃይል ሳይባክን በአግባቡ ለመጠቀም የሚረዳ ነው።
በቀጣይም በሁሉም ማሰልጠኛ ተቋማት አገልግሎቱን ተግባራዊ በማድረግ የሞያ ስልጠና ምደባ ሂደትን በሳይኮሜትሪክ ምዘና የታገዘ በማድረግ ዜጎች በቀጥታ ወደ ሥራ ተሰማርተው በሚወዱት ሞያ ክህሎታቸውን እያሳደጉ መለወጥ እንዲችሉ እየተሰራ ይገኛል።