እንታረቅ --?
=======
ትወደኝ እንደሆን?
አውቃለሁ በመላ፣
ጠላሁሽ አትበለኝ…
ዛ'ሬ ብንጣላ ።
ፀብ በቀን ይሻራል
መውደድ ዘላለም ነው፤
አንተን ከሞት በቀር…
የሚነጥቀኝ ማን ነው ።
በል እስኪ ንገረኝ?
ይቅር የማያስብል ጥፋት ካለ ባ'ዓለም
ሁሉም ሲኦል እንጂ …
ገነት የሚገባ አንዳችም ነ'ፍስ የለም።
እንታረቅ ውዴ?
መለያየት እን'ጣፍ እርቀት እንስፋ?
ለንፋስ አንፍቀድ… …
ሽንቁር ልባችንን ገብቶ እንዳያሰፋ።
እንደዚህ ነው አትበል?
እንደዚያ ነው አትበል?
ከምድር የሚገዝፍ…
ፍቅር ተቀምጦ እኔ'ና አንተ መሀል።
ተጣልተን አንቅር!?
የሚስቀው ሰይጣን ስንታረቅ ያልቅስ?
ፍቅር ያሸንንፋል…
የሰራነው ገደል በይቅርታ ይፍረስ።
Kidus Kass
@betagitim
@betagitim
=======
ትወደኝ እንደሆን?
አውቃለሁ በመላ፣
ጠላሁሽ አትበለኝ…
ዛ'ሬ ብንጣላ ።
ፀብ በቀን ይሻራል
መውደድ ዘላለም ነው፤
አንተን ከሞት በቀር…
የሚነጥቀኝ ማን ነው ።
በል እስኪ ንገረኝ?
ይቅር የማያስብል ጥፋት ካለ ባ'ዓለም
ሁሉም ሲኦል እንጂ …
ገነት የሚገባ አንዳችም ነ'ፍስ የለም።
እንታረቅ ውዴ?
መለያየት እን'ጣፍ እርቀት እንስፋ?
ለንፋስ አንፍቀድ… …
ሽንቁር ልባችንን ገብቶ እንዳያሰፋ።
እንደዚህ ነው አትበል?
እንደዚያ ነው አትበል?
ከምድር የሚገዝፍ…
ፍቅር ተቀምጦ እኔ'ና አንተ መሀል።
ተጣልተን አንቅር!?
የሚስቀው ሰይጣን ስንታረቅ ያልቅስ?
ፍቅር ያሸንንፋል…
የሰራነው ገደል በይቅርታ ይፍረስ።
Kidus Kass
@betagitim
@betagitim