✔️መልስ፦ ከዚህ የተጠቀሱት ክፉዎች መላእክት የሚባሉት መደባቸው ከቅዱሳን መላእክት ሆኖ ነገር ግን ለአምላካቸው ከመቅናታቸው የተነሣ አጥፊዎችን ለመቅጣት የሚፋጠኑ ናቸው። ክፉ ያሰኛቸው ይህ ነው እንጂ በደል በድለው አይደለም። በነገደ ሚካኤል ሥር የሚመሩ ናቸው።
▶️፳. "አቤቱ የተገዳደሩህን መገዳደራቸዉን ለጎረቤቶቻችን ሰባት እጥፍ በብብታቸዉ ክፈላቸው" ይላል (መዝ.78፥12)። በብብታቸዉ ክፈላቸዉ ሲል ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ በብብታቸው ክፈላቸው ማለት በጎረቤቶቻቸው አማካኝነት ፍዳቸውን አምጣባቸው ማለት ነው።
▶️፳፩. "የእንባችንን እንጀራ ትመግበናለህ። እንባችንንም በስፍር ታጠጣናለህ" ሲል ትርጉሙ ምን ማለት ነው (መዝ.79፥5)?
✔️መልስ፦ የእንባችንን እንጀራ ትመግበናለህ ማለት እንባችን የፈሰሰበትን እንጀራ ትመግበናለህ ማለት ነው። እንባችንንም በስፍር ታጠጣናለህ ማለት በኀዘን ሳሉ መጠጥ ሲያቀርቡላቸው እንባቸው በመጠጡ እየፈሰሰ ይጠጡታልና ነው። ይህ ስለ መቃብያን የተነገረ ነው።
▶️፳፪. መዝ.80፥6 ላይ "ጀርባውን ከመስገጃው መለሰ እጆቹም በቅርጫት ተገዙ" ሲል ትርጉሙ ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ ይህ ስለዮሴፍ የተነገረ ነው። ዮሴፍ ጀርባውን ከመስገጃው መለሰ ማለት የግብፅን ጣዖት አለማምለኩን ያመለክታል። እጆቹም በቅርጫት ተገዙ ማለት ዮሴፍ በግብፅ ተሹሞ ሳለ መኳንንቱ ወደ ጣዖቱ እንሂድ ሲሉት እኔማ መች ያደርሰኛል እያለ ቅርጫት ሲያነሣ ሲጥል ይውል ነበርና ይህን ለመግለጽ ነው።
▶️፳፫. መዝ.77፥43 "በጣኔዎስ በረሃ ያደረገውን ድንቁን" ይላል። በጣኔዎስ በረሃ ያደረገው ተአምር ምንድን ነው? በረሃው የት ይገኛል?
✔️መልስ፦ የጣኔዎስ በረሃ በግብጽ ሀገር የሚገኝ በረሃ ነው። ጣኔዎስ የግብጽ አካል እንደመሆኗ እግዚአብሔር በግብጽ ዘጠኝ ተአምራትን አድርጓል።
▶️፳፬. "አፋቸውን በሰማይ አኖሩ። አንደበታቸውም በምድር ውስጥ ተመላለሰ" ይላል (መዝ.72፥9)። ምን ማለት እንደሆነ ቢያብራሩልን?
✔️መልስ፦ አፋቸውን በሰማይ አኖሩ ማለት በአንደበታቸው በሰማይ አምላክ የለም አሉ። አንደበታቸውም በምድር ተመላለሰ ማለት በምድርም አምላክ የለም ብለው ካዱ ማለት ነው። ስለከሓድያን ስለእነ ናቡከደነፆር የተነገረ ነው።
▶️፳፭. "ከሕልም እንደሚነቃ አቤቱ ስትነቃ ምልክታቸውን ታስነውራለኽ" ይላል (መዝ.72፥20)። ትርጓሜው ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ ከሕልም የሚነቃ ሰው ፈጥኖ እንደሚነቃ ጌታ ሆይ ከእስራኤል ክፉዎችን አጥፋቸው ማለት ነው።
▶️፳፮. "የልቤ አምላክ ሆይ ልቤና ሥጋዬ አለቀ። እግዚአብሔር ግን ለዘለዓለም ዕድል ፈንታዬ ነው" ይላል (መዝ.72፥26)። ልቤና ሥጋዬ አለቀ ሲል ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ልቤና ሥጋዬ አለቀ ማለት በፈጣሪዬ አምኜ ነፍሴም ሥጋዬም በክብር ተፈጸመ ማለት ክብር በዛለት ማለት ነው።
▶️፳፯. "አንተ ባሕርን በኀይልኽ አጸናኻት። አንተ የእባቦችን ራስ በውሃ ውስጥ ሰበርኽ" ይላል (መዝ.73፥13)። የእባቦችን ራስ በውሃ ውስጥ ሰበርኽ ሲባል ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ የእባብ ራስ ከተመታ መንቀሳቀስ እንደማይችል በናጌብና በአድማስ መካከል ባለው ውቅያኖስ የምትኖረዋ ሌዋታን የተባለች ፍጥረት ከዚያ ውጭ እንዳትንቀሳቀስ በእግዚአብሔር መወሰኗን ያመለክታል።
▶️፳፰. "ሰው በፈቃዱ ያመሰግንኻልና ከኅሊናቸው ትርፍም በዓልኽን ያደርጋሉ" ይላል (መዝ.75፥10)። ከኅሊናቸው ትርፍም በዓልኽን ያደርጋሉ ሲባል ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ከኅሊናቸው ትርፍ ማለት በልተው ጠጥተው ከተረፈ ገንዘባቸው ሰጥተው በዓልህን ያደርጋሉ ማለት ያከብራሉ ማለት ነው።
▶️፳፱. "ይህ ድካሜ ነው አልኹ። የልዑል ቀኝ እንደ ተለወጠ የእግዚአብሔርን ሥራ አስታወስኹ። የቀደመውን ተአምራትኽን አስታውሳለኹና በምግባርኽም ዅሉ እናገራለኹ። በሥራኽም እጫወታለኹ" ይላል (መዝ.76፥10-12)። የልዑል ቀኝ እንደ ተለወጠ እና በሥራኽም እጫወታለኹ ሲል ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ የልዑል ቀኝ እንደተለወጠ ማለት እግዚአብሔር በሥልጣኑ ሳያጠፋን ማለት ቸርነቱ በዝቶልን ማለት ነው። በሥራህ እጫወታለሁ ማለት አድርግ ያልከኝን ተግባር አድርጌ እኖራለሁ ማለት ነው።
▶️፴. "ከግብጽ በወጣ ጊዜ ለዮሴፍ ምስክር አቆመው። ያላወቅኹትን ቋንቋ ሰማኹ። ጫንቃውን ከሸክም እጆቹንም በቅርጫት ከመገዛት አራቅኹ" ይላል (መዝ.80፥5-6)። ያላወቅኹትን ቋንቋ የተባለው ምን ዓይነት ቋንቋ ነው?
✔️መልስ፦ ይህ ስለዮሴፍ የተነገረ ነው። ዮሴፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ግብፅ ሲሄድ የግባፃውያንን ቋንቋ ባለማወቁ እንደተቸገረ የሚገልጽ ነው።
▶️፴፩. "ከግብጽ ምድር ያወጣኹኽ እኔ እግዚአብሔር አምላክኽ ነኝና አፍኽን አስፋ እሞላዋለኹም" ይላል (መዝ.80፥10)። አፍኽን አስፋ እሞላዋለኹም ማለት ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ አፍህን አስፋ ማለት በጸሎት ለምነኝ ማለት ነው። እሞላዋለሁም ማለት የለመንከኝን አድርግልሀለሁ ማለት ነው።
▶️፴፪. "አቤቱ ፍርድህን ለንጉሥ ስጥ። ጽድቅህንም ለንጉሥ ልጅ። ሕዝብህን በጽድቅ ችግረኞችህንም በፍርድ ይዳኝ ዘንድ። ተራሮችና ኰረብቶች ለሕዝብህ ሰላምን ይቀበሉ" ይላል (መዝ.71፥1-3)። እዚህ ላይ ንጉሥና የንጉሥ ልጅ ያለው ራሱን ዳዊትንና ልጁን ነው?
✔️መልስ፦ አዎ። መዝሙር 71ን ዳዊት ስለልጁ ሰሎሞን ተናግሮታል። ስለዚህ ንጉሥ ያለው ዳዊትን የንጉሥ ልጅ ያለው ደግሞ ሰሎሞንን ነው። በምሥጢር ንጉሥ ያለው አብን የንጉሥ ልጅ ያለው ወልድን ተብሎ መተርጎም ይችላል። ወልድ የአብ የባሕርይ ልጅ ነውና።
▶️፴፫. "የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ። የዓረብና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ" ይላል (መዝ.71፥10)። ይህ በዋናነት ስለ ሰሎሞን ወይስ ስለክርስቶስ የተነገረ ነው? ቢያብራሩልኝ።
✔️መልስ፦ በዋናነት ስለሰሎሞን የተነገረ ቢሆንም ስለክርስቶስም ያስተረጉማል። የነቢያት ቃል አንዱ ብዙ ሐሳቦችን የሚያስተላልፍ ነውና። ለጊዜው ሰሎሞን ጠቢብ ንጉሥ ስለነበረ የተርሴስ፣ የደሴቶች ነገሥታት የተለያዩ ስጦታዎችን አመጡለት ማለት ነው። ስለክርስቶስ ሲነገር ደግሞ ሰብአ ሰገል እጅ መንሻ አመጡለት ማለት ነው።
▶️፴፬. "በምድር ውስጥ በተራሮች ላይ መጠጊያ ይሆናል። ፍሬውም ከሊባኖስ ይልቅ ከፍ ከፍ ይላል። እንደ ምድር ሣር በከተማ ይበቅላል። ስሙ ለዘላለም ቡሩክ ይሆናል። ከፀሐይም አስቀድሞ ስሙ ይኖራል። የምድር አሕዛብ ሁሉ በእርሱ ይባረካሉም አሕዛብ ሁሉ ያመሰግኑታል" ይላል (መዝ.72፥16-17)። የዚህ ንባብ ትርጓሜው ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ የሰሎሞን መንግሥት ለተቸገሩት መጠጊያ እንደሆነ ያመለክታል። ፍሬውም ከሊባኖስ ይልቅ ከፍ ከፍ ይላል ማለት ፍሬ ነገሩ ጥበቡ ከዛፍ ፍሬ ይበዛል ማለት ነው። ሰሎሞን በኢየሩሳሌም ከተማ መኖሩን ለመግለጽ በከተማ ይበቅላል ተብሏል። ስሙ የከበረ ነው ተብሏል። ለክርስቶስ ሲነገር በባሕርይው የሚመሰገን መሆኑን መግለጽ ነው። አሕዛብ ሁሉ ያመሰግኑታል ማለት በእርሱ አምነው ያመሰግኑታል ማለት ነው።
▶️፴፭. "የኃጢአተኞችን ሰላም አይቼ በዐመፀኞች ቀንቼ ነበርና። ለሞታቸው መጣጣር የለውምና። ኃይላቸውም ጠንካራ ነውና። እንደ ሰው በድካም አልሆኑም። ከሰው ጋርም አልተገረፉም" ይላል (መዝ.72፥3-5)። ይህን ንባብ ግልጽ ቢያደርጉልኝ።