አውስትራሊያ ከ16 አመት በታች ያሉ ዜጎቿ ማህበራዊ ሚዲያን እንዳይጠቀሙ ልታግድ ነው።
አሁን ላይ በብዙ ሀገራት ከተደቀኑ ችግሮች መካከል አንደኛው የህፃናት ሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ነው።
የህጻናት የኢንተርኔትና የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ገደብ ካልተበጀለት ወይም ወላጆች ቁጥጥር ካላደረጉ ከፍተኛ የአእምሮ ችግርና የማንነት ቀውስ ሊያስከትልባቸው እንደሚችል ብዙ ጥናቶች አረጋግጠዋል።
አውስትራሊያም የዚህ ችግር ሰለባ ከሆነች ሰነባብታለች። ይህንኑ ችግር በከፍተኛ ሁኔታ ይቀርፋል የተባለ ህግ አውጥታ በፓርላማዋ አጸድቃለች።
ህጉ ከ16 አመት እድሜ በታች የሆኑ ህጻናትና ታዳጊዎች ማህበራዊ ሚዲያ ሙሉ በሙሉ እንዳይጠቀሙ የሚከለክል ነው። ይህንን ህግ ተላልፈው አካውንት ያስከፈቱ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችም እስከ 33 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ቅጣት ይጣልባቸዋል።
TikTok, Facebook, Snapchat, Reddit, X እና Instagram ለህጉ ተገዢ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።
ነገር ግን ብዙ የማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርሞች የተጠቃሚዎቻቸውን እድሜ በትክክል የሚያረጋግጡበት ሁነኛ መንገድ ስለሌለ ይህን ህግ ተግባር ላይ ለማዋል አስቸጋሪ እንደሚያደርገው ይጠበቃል።
ይህ ህግ በዓለማችን የመጀመሪያው ባይሆንም እስከ 16 አመት ላሉ ታዳጊዎች ላይ እገዳ መጣሉ ልዩ ያደርገዋል።
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስቴርም ይህ ሕግ ታዳጊዎች ላይ የሚደርሰውን የማህበራዊ ሚድያ ጉዳት ለመከላከል ይጠቅማል በማለት የዚህን ህግ አስፈላጊነት ገልጸዋል።
ምንም ያህል በርካታ ሰዎች በዚህ ህግ ቢስማሙም አንዳንዶች ግን በማህበራዊ ግንኙነት ላይ ተዕኖ ያሳድራል በማለት ይህንን ህግ ተቃውመውታል።
✍️እናንተስ ስለዚህ ህግ ምን ታስባላችሁ? በሃገራችን ቢተገበር ጥቅም ይኖረዋል?
ሀሰባችሁን comment ላይ አሳውቁን።