የ2017 ዓ.ም የረመዳን ጾምና ኢድ አልፈጥርን ምክንያት በማድረግ በቡና ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት፣ በምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክትና በበረካ ቅርንጫፍ አስተባባሪነት በመዲናዋ ቤተል አለምባንክ አካባቢ በሚገኘው ሙሰዓብ መስጂድ ስር ድጋፍ ለሚሹ ሙስሊም ወገኖቻችን የበዓል ስጦታ በባንካችን ስም ተበርክቷል። በዝግጅቱ ላይ የመስጂዱ ኢማሞችና ኮሚቴዎች፣ የስራ አመራር አባላት፣ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅና ተወካይ ሰራተኞች ተገኝተዋል።