የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሰባት ወራት ከ303 ቢልዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰበ።
****
ይህም በባንኩ ታሪክ የተመዘገበ ትልቁ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን በመሆን ተመዝግቧል።
በባንኩ የተመዘገበውን ይህን ታሪካዊ ስኬት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እና ምክትል ፕሬዚዳንቶች ኬክ በመቁረስ አክብረዋል።
የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ጉባኤ በዛሬው እለት በዋናው መሥሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተጀመረበት ወቅት በተካሄደው በዚህ ስነ ስርዓት ለዚህ ስኬት መመዝገብ ከባንካችን ጋር በመስራት ላይ ላሉ ደንበኞች ትልቅ ምስጋና ቀርቧል።
የተመዘገበው ውጤት ደንበኞች ከባንኩ ጋር ያላቸው ግንኙነት እና የባንኩ የአገልግሎት ጥራት መሻሻል ማሳያ መሆኑም ተገልጿል።
የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ጉባኤው ጥር 26 እና 27 ቀን 2017 ዓ.ም የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች፣ የዲስትሪክት እና ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች በተካተቱበት ከ1200 በላይ በሆኑ ተሳታፊዎች ቀጥሎ የሚካሄድ ይሆናል።