✝️✨ጾመ ገሀድ✨✝️
✨ ከዘጠኙ ዓበይት የጌታ በዓላት ሁለቱ የልደትና የጥምቀት በዓላት ተጠቃሾች ናቸው በሁለቱ በዓላት ቀን ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በኀዘን ማሳለፍ እንደሌለበት ቅዱሳት መጻሕፍት ይናገራሉ ምክንያቱም የክርስቶስ ልደትና ጥምቀት የዕዳ ደብዳቤያችን የተቀደደባቸው የድኅነታችን መሠረት የተጣለባቸው ዐበይት በዓላት ስለሆኑ ነው እነዚህ በዓላት በረቡዕና በዓርብ ቀን ከዋሉ አስቀድመን በዋዜማው ለውጥ አድርገን እንጾማቸዋለን ልደት ረቡዕ ከሆነ ማግሰኞ በዋዜማው፣ ዓርብ ከሆነ ሐሙስ በዋዜማው እስከምሽቱ አንድ ሰዓት (13 ሰዓት) እንጾማቸዋለን በሌሎችም ቀናት በዋዜማቸው በየዓመቱ ይጾማሉ ቀናቱ ሁለት ቢሆኑም ቁጥራቸው ግን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተብለው ነው የሚቆጠሩት፡፡
✨ገሃድ ሁለት መጠሪያ ስሞች አሉት ገሃድና ጋድ፡፡ ገሃድ ማለት መገለጥ መታየት መታወቅ ማለት ነው ተገለጠ ታየ ታወቀ የተባለውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ምንም ከዚያ በፊት አምላክነቱ የተገለጠባቸው ብዙ መንገዶችና ተአምራት ቢኖሩም አብ በደመና ሁኖ የምወደው ልጄ ይህ ነው በማለት፣ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ በመቀመጥ የክርስቶስ አምላክነት የተገለጠበት ዕለት ስለሆነ ገሀድ መገለጥ ተብሎ ተሰይሟል
➦በሌላም በኩል ጋድ ማለት ለውጥ ማለት ነው ልደትና ጥምቀት ረቡዕና ዓርብ ሲሆኑ ለውጥ ሁኖ የሚጾምበት ማለት ነው ስለዚህ ገሀድ ስንል የክርስቶስን አምላክነት በዕለተ ጥምቀት መገለጥ፣ ጋድ ስንል ደግሞ ለዓርብና ለረቡዕ ጾም ለውጥ ሁኖ የተጾመውን ጾም ማለታችን ነው፡፡ ይህንን ጾም ጥር 10 ቀን የሚነበበው ስንክሳር እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፡፡
🕯✨ ✝️መልካም በዓል✝️✨🕯
✨✨✨✨✨✨
✝️#ድምፀ_ተዋህዶ✝️