የደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም ግለሰቡ ከድርጊቱ እንዲታቀብ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።
የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን ቅርጽ በመጠቀም አሸተን በሚል ስያሜ አቶ እንዳለ ተስፋዬ የተባለ ግለሰብ በአሜሪካ የሽቶ ማምረቻ ድርጅት በመክፈት እያሰራጨ መሆኑን ተገልጿል፡፡
ይህም ተግባር የቤተ ክርስቲያኗን መብትና ቅድስና የተዳፈረ እንዲሁም ያለ ገዳሙ ፍቃድ የግሉ የፈጠራ ውጤት አድርጎ በአሜሪካ የአዕምሮ ንብረት ባለቤት አስመዝግቧል ያለው የገዳሙ አሰተዳደር ጽሕፈት ቤት ድርጅቱ ቤተ ክርስቲያኗን ይቅርታ በመጠየቅ ዲዛይኑን እንዲቀይር በጥብቅ አሳስቧል።አባ ሕርያቆስ ጸጋዬ የገዳሙ አስተዳዳሪ በማኅበረ ቅዱሳን ከወልድያ ማእከል ሚዲያ ክፍል ጋር በስልክ ባደረጉት ቆይታ ግለሰቡ ከድርጊቱ እንዲታቀብ ቢጠየቅም ቤተ ክርስታያኗ ፈቃድ ሰጥታኛለች ያለ ሲሆን ይህንንም የሚያረጋግጥ ሰነድ በደብራችን አልተገኘም ብለዋል፡፡
አክለውም ድርጅቱ ከተግባሩ የማይመለስ ከሆነ የቤተ ክርስቲያኗ ክብር እንዲከበር ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን አካላት እና ከሀገረ ስብከቱ የሕግ ክፍል ጋር በመሆን እርምጃዎችን ለመውሰድ እንገደዳለን ሲሉ ተናግረዋል።
በማኅበረ ቅዱሳን
✨✨✨✨✨✨
✝️#ድምፀ_ተዋህዶ✝️
✨✨✨✨✨✨