ዜና ዕረፍት
ከመጀመሪያው ፓትርያርክ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስሊዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ጀምሮ ለ59 ዓመታት በመንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤት በተለያዩ መንፈሳዊ ሥራ ዘርፍ ይሰሩ የነበሩ አባ ናሁ ሠናይ ላዳምጠው ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ ::
በዕድሜ አረጋዊ የነበሩት አባ ናሁ ሠናይ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በጠበልና በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ89 ዓመታቸው የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ,ም ሌሊት ላይ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል፣የአባ ናሁ ሠናይ ላዳምጠው ሥርዓተ ቀብር በመርሀ ቤቴ በርቃቶ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፣በሺህ የሚቆጠሩ ምእመናንና ወዳጅ ዘመድ በተገኙበት ተፈጽሟል ።
የአባ ናሁ ሠናይ ዕረፍት የተሰማንን ኃዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።
ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን አሜን !!!
EOTC
✨✨✨✨✨✨
✝️#ድምፀ_ተዋህዶ✝️
✨✨✨✨✨✨