መካንነት በወንዶች ላይ ሊከሰት ይችላል ?????
መካንነት በወንዶች ላይ ( Male Infertility )
መካንነት የሚባለው ጥንዶች ቢያንስ ለ አንድ ዓመት ያህል ሞክረው (ቢያንስ በሳምንት 3 ጊዜ ያለወሊድ መቆጣጠሪያ) ልጅ መውለድ (ማርገዝ) ካልቻሉ ነው። ነገር ግን ሴቷ ከ 35 ዓመት በላይ ከሆነች በ6 ወር ብቻ ምርመራ ሊጀመርላት ይችላል።
በተደረገው ጥናት መሠረት 85% የሚሆኑ ጥንዶች በመጀመሪያው 12 ወር ውስጥ ሴቷ ትፀንሳለች። የተቀሩት 10% የሚሆኑት ጥንዶች ደግሞ በቀጣዩ አንድ ዓመት ውስጥ ይሳካላቸዋል።
መካንነት የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩት ይችላሉ። ከእነዚህ ውስጥ፤
አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ላይ የሴቷ ችግር፤
አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ላይ ደግሞ የወንዱ ችግር ሲሆን፤የተቀሩት አንድ ሦስተኞቹ ላይ በሴቷም በወንዱም ላይ ችግር ተገኝቷል።
መካንነትን በወንዶች ላይ የሚያመጡ ነገሮች ምን ምንድን ናቸው?
የተለያዩ የጤና ችግሮች በወንዶች ላይ መካንነትን ያመጣሉ። እነዚህ የጤና እክሎች እንዴት መካንነት እንደሚያመጡ ለመረዳት በመጀመሪያ ትክክለኛው የዘር ፍሬ እንዴት እንደሚሠራ እና መጠኑን መረዳት ያስፈልጋል።
የወንድ የዘር ፍሬ የሚመረተው የዘር ከረጢት ውስጥ ነው፡፡ ወንዱ ለዐቅመ አዳም ከደረሰ ጊዜ አንሥቶ በየቀኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዘር ፍሬዎች ይመረታሉ። እነዚህ የዘር ፍሬ ሕዋሳት እንዲመረቱ ቴስቴስትሮን (Testosterone) የሚባል ሆርሞን ዋነኛውን ሚና ይጫወታል። እነዚህ የዘር ፍሬ ሕዋሳት ከተመረቱ በኃላ በአምስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ያድጋሉ። ቀጥሎም በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ ሴሚናል ፈሳሽ ከሚባል ጋር በመደባለቅ በሽንት ቧንቧ አማካኝነት ወደ ሴቷ መራቢያ ክፍል ይገባሉ።
በአማካኝ
በአንድ ግዜ የሚፈስው የዘር ፈሳሽ 1.5 - 5 ሚሊ ሊትር ሲሆን
በአንድ ሚሊ ሊትር ውስጥ የሚኖረው የዘር ፍሬ ብዛት ከ15 ሚሊዮን ይበልጣል፡፡ በጠቅላላው ከ39 ሚሊዮን የሚበልጥ የዘር ፍሬ ሕዋሳትን በውስጡ ይይዛል።
በመጨረሻም ከቁጥሩ በተጨማሪ የዘር ፍሬ ሕዋሶቹ መጠናቸው እና ቅርፃቸው እንዲሁም የሚንቀሳቀሱበት ፍጥነት አስተዋጽዖ አለው።
ከላይ ከተጠቀሰው ሂደት ውስጥ አንዱ ላይ ችግር ከአለ መካንነት ሊከሠት ይችላል። በዚህ ምክንያት የወንዶች መካንነት በተለያዩ ምክንያቶች ሊመጣ ይችላል ማለት ነው። ከ 30 እስከ 40 በመቶ የሚሆነው የመካንነት ችግር የሚፈጠረው ቆለጥ ላይ በሚደርስ ችግር ነው፡፡ ከ 10 እስከ 20 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ከ ዘር ፍሬ ከረጢት ተነሥቶ የሴቷ የመራቢያ አካል እስኪደርስ ባለው መተላለፊያ ቱቦ ላይ በሚደርስ ችግር ምክንያት የሚከሠት ነው።
ይቀጥላል
ምንጭ - wecare
ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ
አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው።
አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።
ስልክ ፦ 0911512338/0913762936
https://t.me/DRLOMBAMOCLINIC