የወባ በሽታ ወረርሽኝ
👉 የወባ በሽታ ምንነት
የወባ በሽታ ኘላዝሞዲየም በሚባል የደም ውስጥ ጥገኛ ተህዋሲ አማካይነት የሚመጣ አደገኛ በሽታ ነው፡፡ሌሎች እንስሳትን የሚያጠቁ ዝርዎችም እንዳሉ ቢታወቅም የሰውን ዘር የሚያጠቃው ኘላዝሞዲየም ፉልሲፓረም፣ኘላዝሞዲየም ቫይቫክስ፣ ኘላዝሞዲየም ኦቫሌ እና ኘላዝሞዲየም ማለሪዬ በተባሉ አራት አይነት ዝርያዎቹ ነው፡፡
👉 የወባ በሽታ መተላላፊያ መንገዶቹ
የወባ በሽታ አኖፌለስ በተባሉ የትንኝ ዝርያዎች እንደሚተላለፍ የሚታወቅ ሲሆን በሴቷ ትንኝ ንክሻ አማካይነትም ከህመምተኛ ወደ ጤነኛ ሰው ይተላለፍል፡፡ የወባ በሽታን የሚያስላልፉት አራት አይነት ብቻ ናቸው፡፡
የወባ በሽታ አስተላላፊ ትንኝ የምትራባው በአብዛኛው በጊዜያዊነት ባቆሩ ውሃዎች ላይ ሲሆን አልፎ አልፎ ዕጮቿ በወንዞችና በሀይቆች ዳርቻ ሊገኙ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪ በመኖሪያ አከባቢ በሚገኙ ዉሃ መያዝ በሚችሉ ቁሳቁሶች ላይ በቀላሉ ትራባለች፡፡
ትንኟ ዕቁላሏን ለማኩረት የሚጠቅማትን ደም ለማግኘት ስትል በሰዎች ጠረን፣ ሙቀትና ትንፋሽ በመሳብና ወደ ሰዎች አካል በመቅረብ ትናከሳለች፡፡ ንክሻው በአብዛኛው በምሽትና (ከምሽት እስከ ንጋት ባለው ጊዜ ውስጥ) በቤት ውስጥ ሲሆን ከቤት ውጭም ይከናወናል፡፤ አኖፊለስ አረቢየንሲስ የተሰኘችው ዋናዋ የወባ አስተላላፊ ትንኝ ቤትም ተመገበች ውጭ በአብዛኛው የምታርፈው በቤት ውስጥ ነው፡፡
**ይቀጥላል**