1. መድኃኒት በትክክል መውሰድ ስንል ምን ማለታችን ነው?
በትክክል ተመርምሮ ለተረጋገጠ በሽታ (በየትኛው የጀርም ዓይነት ወይም በምን ምክንያት እንደመጣ ለተረጋገጠ በሽታ) ትክክለኛው መድኃኒት ለትክክለኛው ታማሚ በትክክለኛው ጊዜና መጠን እና ታማሚውም በባለሙያ የተሰጠውን ምክር ተግባራዊ በማደረግ መድኃኒቱን በትክክል ሲወስድ አግባባዊ የመድኃኒት አጠቃቀም (Rational Medicines Use) አለ እንላለን፡፡ ከእነዚህ ተግባራት ውጭ በሆነ መንገድ ማለትም በትክክል ተመርምሮ የትኛው ዓይነት በሽታ አምጭ ተህዋስ እንዳስከተለው ለማይታውቅ በሽታ፣ ከታዘዘው መጠን በታች ወይም በላይ ሲወሰድ፣መወሰድ ከነበረበት ሠዓት ታልፎ ሲወሰድ፣የታዘዘውን ጸረ-ተህዋስ መድኃኒት ሙሉ በሙሉ ሳይወስድ ከቀረ (ከተቋረጠ)፣ ወዘተ አግባባዊ የመድኃኒት አጠቃቀም የለም እንላለን፡፡መድኃኒትን በአግባቡ አለመጠቀም ደግሞ የተለያዩ ¾Ö?“'ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች ሲኖሩት ከእነዚህ ችግሮች አንዱ የጸረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች መላመድ ነው፡፡
2. ተህዋሲያን (ጀርሞች ) ጸረ -ተህዋሲያን መድኃኒቶችን ይላመዳሉ ይባላል፡፡ ይህ ምን ማለት ነው? ሕመምን የማያድነውስ መቼ ነው ?
የጸረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች መላመድ ማለት ከዚህ ቀደም በበሽታ አምጭ ተህዋሲያን (ጀርሞች) አማካኝነት የሚመጡ በሽታዎችን ለማከም ሆነ ለመከላከል ሲሰጥ የነበረው አንድ ጸረ-ተህዋስ መድኃኒት ሲሰጥ በነበረው መጠን ወይም ከዚያም በላይ የሰውነታችን ሴሎች ሊቋቋሙት በሚችሉት መጠን ሁሉ ሲሰጥ ተህዋሲያኑ የማይሞቱ ወይም መራባትን የማያቆሙ እና ህመምተኛው ከህመሙ የማይፈወስ ከሆነ ተህዋሱ ከመድኃኒት ጋር ተላምዷል ስንል ሂደቱንም የጸረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች መላመድ (Antimicrobial Resistance) እንላለን ፡፡ ስለሆነም መድኃኒቱን በተላመደ ተህዋስ የታመመ በሽተኛ ምንም እንኳን በሽታው በትክክል ታውቆ መድኃኒቱን እየወሰደ ቢሆንም ከበሽታው የማይፈወስ ይሆናል፡፡
3. ከበሽታ አምጭ ተህዋሲያን ጋር የሚላመዱት የትኞቹ የመድኃኒት ዓይነት ናቸው?
እዚህ ጋር መታየት ያለበት ነገር የአንድን መድኃኒት የሚወሰደውን መጠን እየጨመርን ስንሄድ ምላሹ በዚያው መጠን ከፍ የሚል ወይም ያንን መድኃኒት ካልወሰድን ከህመማችን የምንፈወስበት ጊዜ ይኖራል፡፡ ይህ ሂደት መቋቋም (Tolerance) የምንለው ሲሆን ከጸረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች ጋር የተገናኘ አይደለም፡፡ ለምሳሌ የዚህ ዓይነት ባህሪ ከሚያሳዩ መድኃኒቶች የህመም ማስታገሻ መድኃኒቶች እና የአእምሮ ህመም መድኃኒቶች (የናርኮቲክ እና የሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶ) ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የመድኃኒትቶች ከጀርሞች ጋር መላመድ ስንል ግን የሰውነታችን ሴሎች በሚቋቋሙት መጠን ሁሉ ሲሰጥ ከህመማችን የማንፈወስ ስንሆን ነው ማለትም መጠንን መጨመር ወይም መድኃኒቱን መውሰድ ትርጉም አይኖረውም ማለት ነው፤ መድኃኒቱ ከጥቅም ውጭ ሆኗልና፡፡ የጸረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች መላመድ የምንለው ጀርሞች ከጸረ-ተህዋስያን (ጸረ- ጀርም መድኃኒቶች) ጋር በመላመድቸው ምክንያት የሚከሰት ችግርን ብቻ ነው፡፡ ሁሉም የጸረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች ማለትም ጸረ-ባክቴሪያ (አንቲባዮቲክ) መድኃኒቶች፣ ጸረ-ቫይረስ መድኃኒቶች፣ ጸረ-ፈንገስ መድኃኒቶች እና ጸረ-ፐሮቶዝዋ በበሽታ አምጭ ጀርሞ ይለመዳሉ፡፡
4. ተህዋስ መድኃኒቶችን ያለ ሀኪም ትዕዛዝ ገዝተን እንጠቀማለን፣ ጉዳት ይኖረው ይሆን?
በሀኪም ትእዛዝ ብቻ የሚታደሉ መድኃኒቶችን በትክክል ተመርምሮ ላለተረጋገጠ በሽታ መውሰድ ከፍተኛ የጤና፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት አለው፡፡ ህብረተሰቡ ያላግባብ ገንዘቡን ያባክናል፣ መድኃኒቱን በተላመደ ዓይነት በሽታ ይያዛል ፣ይህንንም ለሌሎች ጤነኞች ያስተላልፋል፡፡ ለምሳሌ መድኃኒቱን በተላመድ አይነት የቲቢ በሽታ የተያዘ አንድ ግለሰብ በቀን በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ባክቴሪያውን ሊያስተላልፍ ይችላል፡፡ ከህመም ለማገገም ረጅም ጊዜ ይወስዳል ፣ለረጅም ጊዜ የሆስፒታል ቆይታ ያዳርጋል፣ ከፍተኛ ወጭና የጎንዮሽ ጉዳት ያላቸው መድኃኒቶችን እንድንጠቀም ያስገድደናል፡፡ የዚህ ሁሉ ድምር ውጤት አገሪቱ ለጤና የምታወጣው ወጭ ከፍ እንዲል ያደርጋል፣ ምርትና ምርታማነት እንዲቀንስ ያደርጋል፣ ህብረተሰቡ በጤና ተቋማት አገልገሎት ላይ ያለው አመኔታ እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ ወዘተ፡፡