#AbiyAhmedAli
በቅርቡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የመከረበት ረቂቅ የኤሌክትሮኒክ ግብይት አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ሲጸድቅ በኤሌክትሮኒክ አገልግሎት አማካኝነት የሚፈጸሙ ሁሉንም የግብይት ሂደቶች ለማከናወን የሚቻልበት ደንብ እንዲኖር ያስችላል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ገልጸዋል፡፡
ሕጉ በሁሉም የኮሙኒኬሽን ዘርፎች የሚታየውን የኢንፎርሜሽን እና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፍላጎት መሠረት በማድረግ፣ የመንግሥት እና የግል ተቋማት ዲጂታል አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚችሉበትን ግልጽ ሕጋዊ መሠረት ያበጃል ሲሉ ነው ጠ/ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡
የኤሌክትሮኒክ ንግድ እና የኤሌክትሮኒክ መንግሥታዊ አገልግሎቶች፣ በኤሌክትሮኒክ ግብይት አማካኝነት ዳታን መለዋወጥ እና ማከማቸት፣ ኤሌክትሮኒክ ምዝገባና ፊርማዎች እንደዚሁም የኤሌክትሮኒክ ዳታ መልእክቶች በሥርዓቱ ከተካተቱት አገልግሎቶች ውስጥ ይገኛሉ፡፡
የሕጉ መጽደቅ ከንግድ፣ ከቀረጥ፣ ከሰነድ ማረጋገጥ፣ ከማኅተም፣ ከምስክር፣ ከዲጂታል ክፍያ አኳያ ታላቅ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው የታመነበት ሲሆን የተጠቃሚዎችን መብት ለማስከበርና ዳታ በጥሩ ይዞታ እንዲቆይ ለማድረግም የተሻለ ጥቅም ይሰጣል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ አክለው ገልጸዋል፡፡
@dwamharic_news