#DrTedrosAdhanomGhebreyesus
በሁለት (2) የፈረንሳይ ተመራማሪ ሐኪሞች የተሰጠውን የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ መሞከር አለበት የሚል ሃሳብ የዓለም ጤና ድርጅት ጄነራል ዳይሬክተር " ዘረኛ" ሲሉ ተችተዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም " አፍሪካ ለማንኛውም ክትባት መሞከሪያ አትሆንም፣ መሆንም የለባትም" ብለዋል።
የሕክምና ባለሙያዎቹ ክትባቱ መሞከር ስላለበት ጉዳይ አስተያየት የሰጡት በቴሌቪዥን ይካሄድ በነበረ የቀጥታ ክርክር ወቅት ነው። ይህ የሐኪሞቹ አስተያየት ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን አፍሪካውያንንን " መሞከሪያ አይጥ" አድርጎ ማሰብ ነው ብሏቸዋል።
ከዚህ አስተያየት በኋላ አንዱ ህክምና ባለሙያ ይቅርታ ጠይቀዋል። ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ስለኮሮና ቫይረስ መግለጫ በሚሰጡበት ወቅት ስለጉዳዩ ሲጠየቁ መናደዳቸው ተስተውሏል።
ከዚያም " የቅኝ ግዛት አብሾ" አልለቀቃቸውም ሲሉ መልሰዋል። "በ21ኛው ክፍለ ዘመን ከሳይንቲስት እንዲህ አይነት አስተያየት መስማት የተዋረደ፣ አሳፋሪ ነው።
እንዲህ ዓይነት ነገርን በማንኛውም ሁኔታ እናወግዛለን። እናም የማረጋግጥላችሁ ነገር ይህ በጭራሽ አይሆንም" ብለዋል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
@dwamharic_news