በኮት ዲቮር የተቃውሞ ሰልፈኞች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማእከል አቃጠሉ!
በኮት ዲቮር አቢጃን ከተማ አቅራቢያ በግንባታ ላይ የነበረ የኮሮና ቫይረስ ማእከል በተቃውሞ ሰልፈኞች መቃጠሉን የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል፡፡ ማእከሉን ከማቃጠላቸው በፊት ሰልፈኞቹ ጎማ ሲያቃጥሉ ነበር፡፡
ከአካባቢው የተውጣጡት ሰልፈኞቹ ማእከሉን በሚያቃጥሉበት ወቅት “ማእከሉን አንፈልገውም፤ ቫይረሱን አምጥታችሁብን ልትገሉን ነው” የሚል የተቃውሞ ድምጽ እያሰሙ እንደነበር ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ተቃውሟቸውን ትናንት የጀመሩት ሰልፈኞቹ በዛሬው እለትም ከፖሊስ ጋር ሲጋጩ መዋላቸውም በዘገባው ተካቷል፡፡ በተፈጠረው ግጭት የተጎዳ የለም ተብሏል፡፡ ሀገሪቱ እስካሁን ከ260 በላይ የቫይረሱ ታማሚዎች የተገኙባት ሲሆን ሶስት ሰዎች ሞተዋል፡፡ ማእከሉ በአቢጃን ከሚገነቡ መሰል ማእከላት አንዱ ነው፡፡
ምንጭ፡- አል ዓይን
@dwamharic_news