ዛሬ ጌታ ሥላሴ፣ ለእኔ በመግቦቱ ወደዚህ ምድር እንድመጣ የፈቀደበትና ደግሞም “ኑር!” ብሎ ዘመን የጨመረልኝ ቀን ነው! በአጭሩ የልደት ቀኔ ነው!
ከዘመኔ የሚበልጠውን ከጌታ ጋር አልኖርኹትም፤ የሚበዛው ዘመኔ ያለመታዘዝና ለርሱ ያለ መሰበር ነው፤ ያ ለርሱ ባለመሰበር የኖርኹበት ዘመኔ እጅግ ይጸጽተኛል፤ ዛሬ ግን በጌታ ክርስቶስ ኢየሱስ ጉብኝትና ምጋቤ “ሎሌና ባሪያው ኹኜለት” እያገለገልኹት ነው! ክብር ይግባው! አሜን!
ወደፊት ከምኖረው ዓመታቴ ይልቅ የኖርኩበት የሚበልጥ ይመስለኛል፡፡ እናም በጌታ ቸርነትና መግቦት ቀሪ ዘመኔ፣ ከጌታ ጋር ብቻ ለመኖር እጨክናለኹ! ጌታ ደግሞ በርሱ የተደፉትን በታሪክ ሲጥል አላውቀውምና፣ አዲስ ዐመሉን በእኔ አይጀምርም! ጌታ ኢየሱስ የራሱ የኾኑትን ያውቃል! የዘመናትና የታሪክ ባለቤት የኾንኸው ልዑል ሆይ፤ በጨመርክልኝ ጊዜ ላንተ ብቻ ኖሬ ማለፍን ስጠን፤ አሜን፡፡
My telegram link - https://t.me/ebenezertek