ሕይወት ቴቪን "የእውነት ቃል አገልግሎት" ሊታደግ?
መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ቃል፣ “አትሳቱ፤ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል።” (1ቆሮ. 15፥33) ይላል። “አትሳቱ” የሚባለው ለሚያውቁና ለተረዱ አማኞች ነው። የሚባልበትም ምክንያት፣ የሚያስቱና የሚያሳስቱ ስላሉ ነው። ከክፍሉ እንደምንረዳው በቆሮንቶሳውያን መካከል ትንሣኤ ሙታንን በመናቅና በማቃለል፣ ሕይወትን፤ ዕለታዊ ኑሮን ከመብልና ከመጠጥ ጋር ብቻ ያያያዙትን “አማኞች” ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ካሉት መራቅና ኅብረታቸውን መተው እንደሚገባ ይናገራል። ምክንያቱም ክፉ ባልንጀርነት የመልካሙን ዐመል ስለሚያጠፋ ነው ይለናል። ከበላተኛ ከጠጪ ወይም የሆድን ነገር ብቻ ከሚያወሩ ጋር መዋል፣ ትንሣኤ ሙታንን እንድንንቅ ያደርጋሉና። በሌላ ንግግር የማይገባ ግንኙነት እንደ ጭንቁር እንደሚባላ ማስተዋል እንችላለን።
ይህን እንድል ያደረገኝ፣ ገና ከመከፈቱ "የታደጉኝ" ጥሪ ያቀረበውና ንብረትነቱ የቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የኾነው ቴቪ፣ ምን ገጥሞት ታደጉኝ እንዳለ ለመገመትም ለማመንም ይቸግራል። ቤተክርስቲያኒቱ ሚሊዮናትን ያለፈ አባላትና አማኞች እንዳላት አውቃለኹ። ከወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት የቀደምትነት ሥፍራ ከሚሰጣቸው መካከል ናት። ምናልባትም ለኦርቶዶክሳዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትና ሕይወት እንዲጸናና እንዳይበረዝ በዕቅበተ እምነት ላይ የሚሠሩ፤ እንዲኹም በማኅበራዊ ሕይወትና በሌሎችም ሥራዎች ላይ የሚሳተፉ እንደ ዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌና ጌታሁን ሔራሞ ያሉ “ጉምቱዎችን” ያፈራች ቤተክርስቲያን ናት።
ቤተክርስቲያኒቱ ለተከታዮቿ በቴቪ አገልግሎት መምጣትዋ ይበል የሚያሰኝና እጅግ መልካም ነው። አማኞቿን ይዛ አብነትና ምሳሌነት ያለው ትልቅ ሥራ ትሠራለች፤ በግለኝነትና በከበርቴነት እንደ ፈለጉ ከሚፋንኑ “ነቢይና ሐዋርያ ተብዬዎች” በምታቀርበው ጠንካራ መርሐ ግብር ትኰንናለች፤ በተለየ መንገድ በኅብረትና ብዙዎችን በማሳተፍ የተዋጣለት ሥራ ያቀርባሉ ስንል፤ በጌጃ ያሉትን ከ40 ዓመታት በላይ እስከ ዛሬ ድረስ በዝማሬ የቆዩ እናትና አባቶችን ሕይወትና የአገልግሎት ፍሬአቸውን እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ያሉትን ውብ የወንጌል ምስክርነቶችን ያቀርባሉ ብለን ገና እየጓጓን ሳለ ... ድንገት “ታደጉን” የሚል የድካም ጩኸት አሰሙን። ግን ለምን?
ሕይወት ቴቪ ከኤልሻዳይ ቴቪ ሊማር ይገባዋል። ኤልሻዳይ ቴቪ እንደ ኃይሉ ዮሐንስ፣ ግርማ በቀለና ዘላለም ጌታቸው ላሉ ሐ*ሰ*ተኛ አስተማሪዎች መድረኩን በመክፈት፣ የኢትዮጵያ ክርስትና እንዲቀየጥና እንዲመረዝ የላቀ ሚና ከተጫወቱት የሚመደብ ነው። ሕይወት ቴቪ ከዚህ ከኤልሻዳይ ቴቪ “ስብራት”፣ “እሳት እንደ ነካ ሕፃን” መማሪያ ካልኾነው ከምንም ሊማር አይችልም። አጉል ባልንጀርነት ዳፋውና ጦሱ ብዙ ነውና።
እኔ በግሌ፦ አስተዳደራዊ መዋቅር ቢያስተካክሉ፣ ወደ ሥራ የሚተገበር ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ቢያዘጋጁ፣ አማኞቻቸውን በማስተባበር የገንዘብ አያያዝና አጠቃቀማቸውን ቢያስተካክሉ ... ሌሎችን ታደጉን ከሚል ልመና ነጻ ይወጣሉ ብዬ አምናለኹ። ከዚህ የሚከፋውና የሚያሳዝነው ግን ለትድግና የመጡት አካላት ናቸው። “የእውነት ቃል አገልግሎት” ይባላሉ። መሪያቸው ግርማ በቀለ ይባላል። ስለ “እውነት ቃል አገልግሎት” የተሳ*ሳተ ትምህርትና ልምምድ በአደባባይ ሲናገሩ ከነበሩት አንዱ እኔ ነኝ። እነርሱ ከእነርሱ ውጭ ያሉትን ኹሉ፣ በተለይ ኦርቶዶክስንና ቀደምት ወንጌላውያንን “ጋለሞታዎች” በማለት የሚጣሩ፣ ጤናማ የኾነ የትምህርትም ኾነ፣ የልምምድ ሕይወት የሌላቸው ናቸው። እናም ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ከኤልሻዳይ ቴቪ ተምራ ከቅይጥነት ነጻ እንድትወጣ እመኛለኹ። በርግጥ “ጋለሞታ” ወደሚሏት ቤተክርስቲያን ሊጠቅሟት አልመጡም።
የተሐድሶ አገልግሎትን በትምህርታቸውና በልምምዳቸው ከሚያዳክሙና በተጣ*መመ ትምህርታቸው ወደ ዓለማዊነት ከሚነዱት መካከል ቀዳሚዎቹ “የእውነት ቃል አገልግሎት” ቡድኖች ናቸው። የሚያሳዝነውና ልብ ሰባሪ ሥራቸው፣ የሚያጠምዱት “የዳኑትንና ወደ ጌታ የመጡትን” እንጂ ሌሎችን አያጠምዱም። እናም ቃለ ሕይወታውያን በቃለ ጥፋት እንዳትወረሱ ለራሳችኹ ተጠንቀቁ።
“ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ባለመጥፋት ከሚወዱ ሁሉ ጋር ጸጋ ይሁን፤ አሜን።” (ኤፌ. 6፥24)
My telegram link - https://t.me/ebenezertek
My blog link -http://abenezerteklu.blogspot.com/2025/02/blog-post_68.html
My youtube link - http://www.youtube.com/@-abenezertekludiyakon8842