የአባ ገብርኤል ጉዳይ የሃይማኖትና የጽድቅ ቅንአት እንዳልኾነ እኒህ ማሳያዎች ናቸው፦
- "እንኳን ማማለድ ማርያም አፍርሳ መሥራት ትችላለች" ብሎ ሄኖክ ኃይሌ ሲናገር ማንም ትንፍሽ አላለም፣
- አንዱ ጳጳስ፦ "ድንግል ማርያም ባትኖር እግዚአብሔርም ክርስቶስም የሉም" ብለው በአደባባይ ተናግረው አንድም የኦርቶዶክስ ሊቅም ኾነ አክቲቪስት ቲክቶዶክሶች አቧራ አላቦነኑም! ለምን?
- አንዱ የነገረ መለኮት ምሩቅ ነኝ ባይ፣ "ያለ ድንግል ማርያም አማላጅነት ዓለም አይድንም" ብሎ ከኦርቶዶክስ ነገረ መለኮት ኮሌጅ ተመርቆ ሲወጣ፣ ማን መምህር፣ የቱ ኮሌጅ፣ ማንኛው ሲኖዶስ፣ የትኛው ሰንበት ተማሪና ሊቅ ስለ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ በአደባባይ መነቀፍ ቆረቆረው፤ ከነከነው?!
- ዘበነ ለማ፣ "ሰይጣን ከክርስቶስ ይልቅ ማርያምን ይፈራታል" ሲል እንዴት፤ በየት በኩል ማንም አላለም!
- በድጋሚ ዘበነ ለማ፣ "የዶሮ 12ቱ ብልቶች የኢየሱስ ደቀመዛሙርት ምሳሌ ነው" ብሎ ሲዘብት ማን ምን ተናገረ?!
- ምሕረተ አብ አሰፋ "ኦርቶዶክስ እንጂ ክርስቲያን አይደለንም" ብሎ ክርስትናን ሲያጥላላ፣ ማን ነበር "ኦርቶዶክስ ትምህርት እንጂ "ተቋም" አይደለም" ያለ?!
...
ብዙ ክርስቶስንና መጽሐፍ ቅዱስን የሚያዋርዱ ትምህርቶች በአደባባይ ሲሰጡ ማንም ምንም አላለም። እኒህንና ሌሎችንም አያሌ የኑ-ፋ-ቄ ትምህርቶች የሰጡ አካላት ዛሬም በኦርቶዶክስ "ዐውደ ምሕረቶች" ያለ ጠያቂ አሉ። ግና የአባ ገብርኤል ነገር መግነኗ ብዙ ጥያቄ እንድጠይቅና፣ "ኢየሱስን ማንኳሰስ ችግር የለውም፤ ማርያምና ታቦቱ እስካልተነካ" ድረስ ብለን እንድንናገር ያስደፍረናል። የሲኖዶሱን ውሳኔ እየጠበቅን፣ ኦርቶዶክስ ሆይ፤ መንፈስ ቅዱስ መመለስን እንዲሰጥሽ በብዙ እንመኛለን ማለትን አንተውም።