😘ድህነት ምንድነው??
ድሀ ስትሆኑ ማንም አይፈልጋችሁም
ማንም አያዳምጣችሁም ለሰው ልጅ ያለውን ክብር እራሱ አይሰጧችሁም አይወዷችሁም ድህነታችሁን መቀየር እንደምትችሉ አያምኑም ሊወዷችሁ ሊሰሟችሁ አይፈልጉም
የእግዜሩን ሰላምታ እራሱ ላለውና ለሌለው ሰው እኩል አይደለም እሚሰጡት በጣም ይገርመኛል የተማረው ሙህሩ ቁጭ ብሎ ድሃ ስለሆነ ብቻ በገንዘብ የካበተ ግን ያለውን ገንዘብ እንኳን እንዴት መጠቀም እንዳለበት እማያቀውን የአሰተሳሰብ ደሃ የሆነው ሲሰግዱና ምንም እውቀት ሳይኖረው አለምን እንደሚቀየር ሲያስቡ ግን እማይገባኝ ከገንዘብ በፊት ሰው አይደል እንዴ የተፈጠረው?? ሰው በማንም በምንም አይፈጠረም አልተፈጠረም። ለምን መፈጠር እሚችለው ሰው አድርጎ በአምሳሉ ፈጠሮ እዚች ምድር ላይ ያመጣው እግዚአብሔር ብቻ ነው እሚችለው ። ከዛ በመፈለግነው መንገድ መሄዱ ደግሞ የኛ ምርጫ ነው ።
ከፈጣሪ ውጭኮ ደሀን እሚወድ የለም ሌላው ቀርቶ የስጋ ዘመድንኳን ያለውን ነው እሚወዱት ፣ አዳንዴ ሰዎችን እንዲህ ገፍተን ገፍትን ክፉ እምናደርጋቸው እኛው እራሳችን ነን ደሀም ሰው ሀብታምም ሰው እኩል ናቸው፣ ሀብታምም ሀብታም ሆኖ አልፈጠረም አብቱን ፈጠረው እጅ ፣ደሀውም ደሀ ሆኖ አልተፈጠረም ድህነቱን ይቀይራል ደሀ ሆኖ አይቀርም ምናልባት የመቅደም የመቀደም ይሆን ይሆናል እጅ ማንም የነበረበት ላይ አይቀርም እና የገንዘብ ድህነት እና የአሰተሳሰብ ድህነት እናስወግድ የዕለቱ መልዕክታችን ነው!!!
@eec1227