በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ የስርቆት ወንጀል የፈፀመዉ ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተያዘ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ዳዉሮ ዞን ዲሳ ወረዳ ጋቶ ጉፎ ቀበሌ ከጎራ እስከ ዲሳ እየተዘረጋ በሚገኘዉ የኤሌክትሪክ ማስፋፊያ መስመር ላይ ጨለማን ተገን በማድረግ የስርቆት ወንጀል የፈፀመው ግለስብ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው በዉድ ዋጋ ወደ ሃገር የገቡ የኤሌክትሪክ የመስመር ሽቦችን በመስረቅ በእንሰት ቅጠል ስር ሲደበቅ የተመለከቱ የህብረተሰብ ክፍሎች ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ ነው፡፡
ተጠርጣሪዉ ላይ የተጀመረው ምርመራ የቀጠለ ሲሆን ምርመራው ሲጠናቀቅ ለዓቃቤ ህግ ተልኮ ክስ የሚመሰረትበት ይሆናል፡፡
በኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማቶች ላይ የሚፈፀምን የስርቆት ወንጀል መከላከል የሁሉም ሃላፊነት በመሆኑ መሰል እኩይ ተግባራትን የሚፈፅሙ አከላትን ሲመለከቱ በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት ማሳወቅና ጥበቃ ማድረግ ይገባል።
መረጃው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ፓሊስ ኮሚሽን ነው!!
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት