መጪውን የገና በዓል አስመልክቶ የተደረገ ቅድመ ዝግጅት
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት በቅድሚያ መልካም ምኞቱን ይገለፃል፡፡
ተቋሙ በበዓሉ ዋዜማና በዕለቱ ሊያጋጥም የሚችለውን የኃይል መቆራረጥና መዋዥቅ ችግር ለመቀነስ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
በበዓሉ ዋዜማና በዕለቱ የኃይል መቆራረጥና መዋዥቅ ችግር ሳይፈጠር ለተጠቃሚው ለማቅረብ ከተከሰተም በአፋጣኝ የአስቸኳይ ጥገና ስራ ለመስራት በየደረጃው ግብረ-ሃይል በማዋቀርና አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በማዘጋጀት ወደ ስራ ገብቷል፡፡
ግብረ-ሃይሉም በተደጋጋሚ የኃይል መቆራረጥና መዋዠቅ ችግር የሚስተዋልባቸውን መስመሮች በመለየት የቅድመ መከላከል ጥገና ስራዎች እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር በመቀናጀትና የጋራ ግብረ ሀይል በማዋቀር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በጋራ እየተከናወኑ ነው፡፡
የቅድመ-ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ደግሞ በዓሉ ሲደርስ የሚኖረውን አላስፈላጊ እንግልት ለማስቀረት ከወዲሁ የኤሌክትሪክ ኃይል አስቀድመው እንዲገዙ /ካርድ እንዲሞሉ/ እየጠየቅን፤ በዋዜማውና በዕለቱ ካርድ ማስሞላት ለሚፈልጉ ደንበኞችም የተለዩ ማዕከላት ይህንን አገልግሎት እንደሚሰጡ እንገልፃለን፡፡
ደንበኞች የኃይል አጠቃቀም ለአደጋ ተጋላጭ እንዳያደርጋቸው አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እየጠየቅን፣ የኃይል ጭነት በማይበዛባቸው ሰዓታት በተለይ ከምሽቱ 3፡00 እስከ ንጋቱ 11፡00 ባሉት ጊዚያት መጠቀም የተሻለ የኤሌክትሪክ ኃይል ከማግኘት ባለፈ ሊኖር የሚችለውን የኃይል መቆራረጥ ችግር ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ለማስገንዘብ እንወዳለን፡፡
የታደሰ የተቋሙ መታወቂያና የስራ ትእዛዝ ደብዳቤ የያዙ የቴክኒክ ባለሞያዎቻችን በተለያዩ አካባቢዎች ለስራ ጉዳይ እንደሚንቀሳቀሱ እያሳወቅን፤ ሆኖም የተቋሙ ሠራተኞች በመምሰል መሠረተ ልማቱ ላይ ስርቆትና ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ አካላት ሊኖሩ ስለሚችሉ፤ህብረተሰቡ ይህንን ከወዲሁ ተገንዝቦ የኤሌክትሪክ መሰረት ልማቶችን እንዲጠበቅና አጠራጣሪ ነገር ካጋጠመው ለፀጥታ አስከባሪ አካላት ወይም ለተቋማችን ጥቆማ እንዲሰጠን በዚህ አጋጣሚ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
በመጨረሻም ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር ተያይዞ ማንኛውም ቅሬታ፣ ጥቆማና አስተያየት በ905 ወይም 904 ነፃ የጥሪ ማዕከል በመደወል፣ በአቅራቢያዎ በሚገኝ የአገልግሎት ማዕከላችን በቀጥታ ስልክ በመደወል ወይም በአካል ማቅረብ እንደሚችሉ እናሳውቃለን፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት