የተቋሙ የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተጀመረ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መካሄድ ጀመረ፡፡
ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተቋሙ በግማሽ አመቱ ያከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት፣ የታዩ ጠንካራ ጎኖች፣ ያጋጠሙ ችግሮች እንዲሁም የተቋሙ የቀጣይ የትኩረት መስኮች ላይ ውይይት የሚደረግ ይሆናል፡፡
በተጨማሪም የበጀት ዓመቱ የተቋሙ የሶስት ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድ ማጠናቀቂያ ዓመት በመሆኑ በዕቅድ በአፈፃፀሙ ላይ ውይይት የሚደረግ ይሆናል፡፡
ዛሬ የተጀመረው የዕቅድ አፈፃፀም መድረክ ተቋሙ አዲስ የአሠራር ስርዓት ማሻሻያ ተግባራዊ ካደረገ በኋላ እየተካሄደ ያለ የመጀመሪያ መድረክ ነው፡፡
በዚህም ሁሉም ሥራ አስፈጻሚዎች የመጀመሪያውን መንፈቅ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ካቀረቡ በኋላ ውይይት ተደርጎ የቀጣይ አቅጣጫም እንደሚቀመጥ ይጠበቃል፡፡
በግምገማ መድረኩ የተቋሙን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክቡር ኢንጂነር ሽፈራው ተሊላን ጨምሮ ሥራ አስፈፃሚዎች፣ የሪጅን አስተባባሪዎችና ዳይሬክተሮች እንዲሁም የመሠረታዊ ሠራተኞች ማህበር ሰብሳቢን ጨምሮ ሌሎች የስራ አመራሮችም ተሳታፊዎች ናቸው።
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት