የኃይል ስርቆት በፈፀሙ ግለሰቦች ላይ እርምጃ ተወሰደ
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ቆጣሪዎችን በመነካካት የኃይል ስርቆት በፈፀሙ የወፍጮ ቤት፣ የዳቦ እና የእንጀራ መጋገሪያ ቤት ባለቤቶች ላይ እርምጃ ወስዷል፡፡
በዚህ በጀት አመት ብቻ 18 ዘመናዊ ቆጣሪዎች ላይ የኃይል ስርቆት የተፈፀመ ሲሆን ሪጅኑ በስርቆት ያጣውን ከ4 ሚለየን ብር በላይ የኃይል ፍጆታ ሂሳብ ገንዘብ ማስከፈሉን በሪጅኑ የኢነርጂ ማኔጅመንት ኃላፊ አቶ ለሚ አዱኛ ተናግረዋል፡፡
አቶ ለሚ አክለውም 11 ሥርቆት የፈፀሙ ድርጅቶች ላይ ከ5 ሺህ እስከ 10 ሺህ ብር ቅጣት እንዲቀጡ ማድረጉንና በስርቆት ወቅት ለተበላሹ ቆጣሪዎች 18 ሺህ ብር እንዲከፍሉ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
የኃይል ስርቆት መረጃው የተገኘው ተቋሙ በሚጠቀመው መተግበሪያ አማካኝነት ሲሆን በዚህ ዓመት ብቻ በኃይል ሥርቆት ላይ በተሳተፉ ስምንት ደንበኞች ላይ ክስ ተመስርቶ ክትትል እየተደረገባቸው እንደሆነና ሦስቱ በሂደት ላይ መሆናቸውን ሃላፊው ተናግረዋል፡፡
ተቋሙ የንባብ ጥራት ለመጨመር እና የኃይል ስርቆትን ለመከላከል ዘመናዊ ቆጣሪዎችን እየተገበረ ሲሆን የፍጆታ የንባብ ጥራት ለመጨመር እና የኃይል ስርቆትን ለመከላከል የዘመናዊ ቆጣሪዎችን እየተገበረ የሚገኝ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት