የቦሌ ለሚ አራብሳ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሃይል አቅርቦት ችግር ተፈታ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቦሌ ለሚ አራብሳ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እና በአካባቢው ይስተዋል የነበረው የኃይል መቆራረጥ ችግር መቅረፍ መቻሉን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ዋቅጅራ ገልፀዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አክለውም በአካባቢው ይስተዋል የነበረውን የሃይል መቆራረጥ ችግር መቅረፍ የተቻለው የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ማስፋፊያ ግንባታ በመደረጉ ነው ብለዋል፡፡
ለአካባው 5 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር ባለ ጥንድ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ እና 96 የኮንክሪት ምሰሶ ተከላ ስራ መከናወኑን አቶ ብርሃኑ አስታውቀዋል፡፡
የተዘረጉት የኤሌክትሪክ መስመር ሽፍን በመሆናቸው በዝናብ እና በንፋስ ወቅት በሽቦዎች መቀራረብ እና መነካካት የሚፈጠርን የኃይል መቆራረጥ ችግር መቆራረጡን መቀነስ ተችሏል፡፡
የአሌክትሪክ መስመር ማስፋፊያ ሥራውን ለማጠናቀቅ አንድ ወር ጊዜ የፈጀ ሲሆን የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቱን ለመዘርጋት ከ17 ሚለየን ብር በላይ ወጪ መደረጉን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡
ቀድሞ የነበረው የኃይል መቆራረጥ ችግር ተማሪ ለመሸኘት፣ ለማንበብ፣ ምግብ ለማብሰል እንዳስቸገራቸው በአካባቢው የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተናግረዋል፡፡
ነዋሪዎቹ ከበዓል ወዲህ የተቋሙ የስራ ሃላፊዎች ችግሩን ተረድተው በሰጡት አቅጣጫ መሰረት በአከሳባቢው ይስተዋል የነበረው የኃይል መቆራጥ ችግር መቀረፉን ተናግረው በዚህ መልኩ በወጥነት ሊቀርብላቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት