መንግስት በተያዘው አመት "የሃይል አማራጭን በመጠቀም ፖለቲካዊ ፍላጎቶችን ለሟሟላት የሚደረጉ ጥረቶችን አይታገስም” - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
"የሃይል አማራጭን በመጠቀም ፖለቲካዊ ፍላጎቶችን ለሟሟላት የሚደረጉ ማናቸውንም እኩይ ተግባራት መንግስት በልበ ሰፊነት የሚያልፍበት ዕድል እጅግ የጠበበ ነው" ሲሉ አዲስ የተመረጡት #የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ አስታወቁ።
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሂዷል።
የቀድሞዋ ፕሬዝዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የመጨረሻ የመክፈቻ ንግግር የሚጠበቅበት የሁለቱ ምክር ቤቶች ሥብሰባ ቢጠናቀቅም የቀድሞዋ ፕሬዝዳንት ምንም አይነት ንግግር ሳያደርጉ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሆነው ሲያገለግሉ ለነበሩት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ሃላፊነታቸውን አስረክበዋል።
በዚሁ ወቅት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ታዬ አጽቀሥላሴ የመንግስትን ቀጣይ አመታዊ አቅጣጫ በሚያመላክተው ንግግራቸው “ከእንግዲህ በኢትዮጵያ ምድር ሃይልን በብቸኝነት መጠቀም መብት የመንግስት ተቋማት ብቻ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል” ብለዋል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ