"የትግራይ ፖለቲካ ወደባሰ ሁኔታ እየተጓዘ ነው" – ጌታቸው ረዳ
የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ፤ የህዝብን ሰላምና ደህንነት ከግምት ውስጥ ያላስገባ በወንበር ላይ የተመሰረተ ግጭትና ትርምስ እየተፈጠረ መሆኑን ገለፁ።
አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ "ለረጅም ጊዜ ስልጣን ላይ የቆየው ሃይል" በማለት የጠቀሱትን ቡድን “ሁሉንም ነገር አፍኖ ወደ ስልጣን ለመመለስ እየሰራ ነው ብለዋል።
ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች ወደጎን በማለት “ወንበራችን ተነጠቅን” የሚሉ አካላት “በጉልበት እንመልሳለን” ወደሚል እንቅስቃሴ መግባታቸውን ገልፀዋል። "ጉባኤውን አከናውኛለሁ በማለት የሚንቀሳቀሰው ሃይል በጠላትነት ከፈረጀው ሀይል ጋር በመተባበርም ወንበር ለመያዝ ሌት ተቀን እየሞከረ ነው" ብለዋል አቶ ጌታቸው።
በመሆኑም የትግራይ ፖለቲካ ወደ ከፋ ሁኔታ እየተጓዘ መሆኑን ገልፀዋል። “በዞኖችና ወረዳዎች ስርዓት የሌለው ህገወጥ አሰራር እየተሰራ ነው” ብለዋል።
"የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመመለስ እና የትግራይን ፀጥታ ከማረጋገጥ ይልቅ ወደ ሌላ የስልጣን ሽኩቻ እንድንገባ ተገድደናል" ሲሉ ገልፀዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ እንዳሉት፤ የተካሄደው ጉባኤ በፓርቲው አሰራርም ሆነ የፌዴራል መንግስት ባወጣው መመሪያ ህገወጥ ነው ብለዋል። ልዩነቶች በዕርቅና በድርድር ለመፍታት እርሳቸውና ጓቻቸው ዝግጁ መሆናቸውም በመግለጫቸው ተናግረዋል።“እንደ ህወሐት መዳን ከፈለግን በራሳችን ውስጣዊ አቅማችን እንጂ በውጪ ሃይሎች መሆን የለበትም” ብለዋል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ