በቱርክ በደረሰ ፍንዳታ የ12 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በሰሜን-ምዕራብ ቱርክ ባሊኬሲር ከተማ በአንድ የጦር መሣሪያ እና ፈንጂ ፋብሪካ ውስጥ በደረሰ ፍንዳታ የ12 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በአራት ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ፡፡
የአዳጋው መንስዔ አለመታወቁን እና ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት ሁኔታውን መቆጣጠር መቻሉን የቱርክ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ዬርሊካያ ተናግረዋል፡፡
አደጋውን ተከትሎ የእሳት አደጋ ቡድንን ጨምሮ የደኅንነት እና የጤና ባለሙያዎች ወደ ስፍራው ማምራታቸውን የገለጹት ደግሞ የባሊኬሲር ከተማ ከንቲባ ኢስማኤል ኡስታኦግሉ ናቸው፡፡
የአደጋውን መንስዔ ለማወቅ ተጨማሪ ምርመራዎች እየተደረጉ ነው ማታቸውን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ፍንዳታው ባስከተለው የእሳት ቃጠሎም የፋብሪካው ግማሽ ክፍል መውደሙን ከተንቀሳቃሽ ምስሎች ለማየት ተችሏል፡፡