የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም ዛሬ ባደረጉት ንግግር የትራምፕን ውሳኔ ተችተዋል፡፡ ፕሬዘደንት ትራምፕ አሜሪካ ከጤና ድርጅቱ መውጣቷንና የምታደርገውን ድጋፍ ማቆሟን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
ዶክተር ቴዎድሮስ በድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ ቦርድ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር ‹‹በዚህ ውሳኔ እጅግ አዝነናል፡፡ አሜሪካ ይህንን መለስ ብላ እንደምታጤነው ተስፋ አለኝ›› ብለዋል፡፡ ትራምፕ በውሳኔያቸው ላይ የአለም ጤና ድርጅት ፈጣን የማሻሻያ እርምጃዎችን እንዳልወሰደ የጠቀሱ ቢሆንም ዶክተር ቴዎድሮስ ግን በዛሬ ንግግራቸው ‹‹የአለም ጤና ድርጅት ባለፉት ሰባት አመታት በታሪክ ውስጥ እጅግ ጥልቅና ሰፊ ማሻሻያዎችን አድርጓል›› ብለዋል፡፡
ትራምፕ ይህ ድርጅት ፍትሀዊ ባልሆነ ሁኔታ ከአሜሪካ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚፈልግ ገልፀው የነበረ ሲሆን ዶክተር ቴዎድሮስ በበኩላቸው በዛሬ ንግግራቸው ሌሎች የገንዘብ ምንጮችንና ለጋሾችን ሲፈልጉ መቆየታቸውን ገልፀዋል፡፡
የኮቪድ ወረርሽኝን በተመለከተም ድርጅቱ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰዱን ጠቅሰው በአሰራራቸው ላይ ፈተናዎችና ድክመቶች መኖራቸውን የገለፁት ዶክተር ቴዎድሮስ ድርጅታቸው ለሁሉም አገራት ያለማዳላት እንደሚሰራም መናገራቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
Via : ዘ-ሐበሻ