ጾታዊ ጥቃትን ለመከላከል ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል የድርሻውን ሚና እንዲወጣ ተጠየቀ።
===========================
(ታህሳስ 30/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞች ዓለም አቀፍ የነጭ ሪቫን ቀንን ምክንያት በማድረግ ውይይት አካሂደዋል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛና በአገራችን ለ19ኛ ጊዜ “የሴቷ ጥቃት የኔም ነው ዝም አልልም!!” በሚል መሪ ቃል በተከበረው ቀን ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ምህረተክርስቶስ ታምሩ በውይይት መድረኩ ባቀረቡት ገለጻ ከጊዜ ወደ ጊዜ በተፈጠረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች መሻሻሎች ቢኖሩም በማህበረሰባችን ላይ በርካታ ጾታዊ ጥቃቶች እየተፈጸሙ መሆኑን ጠቅሰው ይህንንም በሚገባ ለማስቆም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ሚኒስቴር መ/ቤቱም ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በአጠቃላይ ትምህርትም ሆነ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚተገበር የጸረ ጾታዊ ጥቃት መመሪያ አዘጋጅቶ ወደ ሥራ ማስገባቱን አንስተዋል፡፡
ወ/ሮ ምህረተክርስቶስ ጨምረውም ጾታዊ ጥቃቶች እንዳይፈጸሙ መከላከልና ግንዛቤ መፍጠር የመጀመሪያ ርምጃ መሆኑን ጠቅሰው ተፈጽመው ሲገኝ ለተጠቂው አካል የህክምና፣የሥን፟ልቦናና የፋይናንስ ድጋፍ ከማድረግ ጎን ለጎን አጥቂው አካል የሚፈጸመውን ወንጀል የሚመጥን ቅጣት እንዲያገኝ መሥራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
በውይይት መድረኩ የተገኙ ወንዶች ጾታዊ ጥቃትን ለመከላከል ነጭ ሪቫን በማድረግ ቃል የገቡ ሲሆን በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ውይይት ተካህዶ፣ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
የነጭ ሪቫን ቀን ቀደም ሲል በትምህርት ማህበረሰቡ ሲከበር የቆየ ሲሆን ይህ የማጠቃለያ ውይይት መድረክ መሆኑ ተገልጿል።