በትምህርት ቤትና አካባቢው የሚፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶችን በጋራ የመከላከልና ምላሽ የመስጠት ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።
------------------------------
(የካቲት 3/2017 ዓ.ም) በትምህርት ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ በትምህርት ቤትና አካባቢው የሚፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶችን የመከላከልና ምላሽ የመስጠት አቅምን ለማጎልበት እንዲቻል ለባለድርሻ አካላት የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጥቷል።
በመድረኩ የተገኙት የስራ ክፍሉ ሃላፊ ወ/ሮ ምህረተክርስቶስ ታምሩ በትምህርት ቤትና አካባቢው የሚፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶችን በጋራ የመከላከልና ምላሽ የመስጠት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ይህንን ስራ ከፍ ለማድረግ የባለድርሻ አካላትን የነቃ ተሳትፎ ጠይቀዋል።።
የሥልጠናው ዓላማ ትምህርት ቤቶች ውስጣቸውንና አካባቢያቸውን ከጾታዊ ጥቃቶች ነጻ በማድረግ ሴቶችና ህጻናት ትምህርታቸውን በውጤታማነት የሚከታተሉበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠርና ለሚከሰቱ ጾታዊ ጥቃቶችም አፋጣኝ ምላሽ መስጠት የሚያስችል አቅም ለመፍጠር መሆኑ ተገልጿል።
ወ/ሮ ምህርተክርስቶስ ጨምረውም ሥልጠናው ሴቶችና ህጻናት ከትምህርት ቤት እንዳይቀሩ፣ሳይሽማቀቁ ትምህርታቸውን እንዲማሩ፣ያለእድሜ ጋብቻና ለሌሎች ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችም እንዳይጋለጡ የባለድርሻ አካላትን ግንዛቤ በማሳደግ የድርሻቸውን እንዲወጡ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በሥልጠናው ከትምህርት ሚኒስቴር፣ከክልልና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች እና በአገር አቀፍ ደረጃ በናሙናነት ከተመረጡ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የሥርዓተ ጾታ አስተባባሪዎችና ርእሳነ መምህራን ተሳታፊዎች ሆነዋል፡፡
=====///====