በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚካሄዱ የጥናትና የምርምር ስራዎችን ጭብጥ ተኮር ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ።
-------------------------------------
(ጥር 04/2017 ዓ.ም) በጭብጥ ተኮር (Thematic) ምርምር ፈንድ አስተዳደር ትግበራ ላይ ያተኮረ ግምገማዊ ስልጠና በትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ተካሂዷል።
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በአገሪቱ በርካታ ምርምሮች እየተካሄዱ ቢሆንም ከውጤት ጋር ተያይዞ በርካታ ጥያቄዎች ይነሳሉ።
በተበጣጠሰ መንገድ የሚካሄዱ የጥናትና ምርምር ስራዎች የሚፈለገውን ውጤት እያመጡ አለመሆኑንም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመዋል።
በመሆኑም የፋይናንስ ሀብትን በተገቢው መንገድ ለመጠቀም የምርምር ርዕሶችን ማሰባሰብና ተጨባጭ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ምርምሮችን በማሰባሰብ ተጨባጭ ለማድረግ ሚካሄደውንም ተግባር ትምህርት ሚኒስቴር ከጎናቸው መሆኑንንም አቶ ኮራ ተናግረዋል።
የምርምርና የማህበረሰብ ጉድኝት ተጠባባቂ መሪ ስራ አስፈጻሚ ሠራዊት ሀንዲሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው የ ‘thematic’ (ጭብጥ ተኮር) የምርምር ፈንድ አስተዳደር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በመተግበር ላይ መሆኑን አመልክተዋል።
የሪፎርሙ ዋነኛ ዓላማም የምርምር አደረጃጀትን ተገቢነት፣ ውጤታማነት እና ዲጂታላይዜሽን በማሳለጥ የሚካሄዱ ጥናቶች ወጪ ቆጣቢና የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ እንዲሆኑ ማስቻል መሆኑን ጠቁመዋል። ፈጠራን ማበረታታት የሪፎርሙ ሌላኛው ዓላማ መሆኑንም ዶ/ር ሰራዊት ጨምረው ገልጸዋል።
በግምገማዊ ስልጠናው ላይ ከሁሉም የመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ምክትል ፕሬዚዳንቶች እና ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል።