በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ የተመራ የከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ ከኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ጋር የአገራችንን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን በጋራ መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በስፋት መክረዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ ኢትዮ ቴሌኮም የአገር ኩራትና ምልክት መሆኑን በመግለጽ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ግንባር ቀደም ሚና በመጫወት እንዲሁም በዲጂታል አገልግሎቶች እና ቴሌብር አስደማሚ ውጤት በማስመዝገብ ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አክለውም የዲጂታል አገልግሎት ተደራሽነትና አካታችነት በመጨመር ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በሚያስችሉ የኢጋቨርንመንት፣ ኢኮሜርስ፣ ኢኖቬሽን፣ በጀማሪ የሥራ ፈጠራ፣ ጥናትና ምርምር፣ ስማርት ስልክ ስርጸት እና የዲጂታል ክህሎትን ለመሻሻል በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል ኢትዮጵያን ጉዞ ለማሳካት ያከናወናቸውን በተለይም ገጠራማ አካባቢዎችን ጨምሮ ለዜጎች የዲጂታል መሠረተ ልማት ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም በቴሌብር ዲጂታል መፍትሔዎች፣ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች እና ማኅበራዊ ኃላፊነት ስላከናወናቸው ተግባራት ሰፊ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ልዑካን ቡድኑ የኩባያችንን ኤክስፒሪየንስ ማዕከል የጎበኙ ሲሆን የስማርት ሲቲ ፕሮጀክትን ጨምሮ እንደ ግብርና፣ ትምህርት፣ ጤና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ትራንስፖርት፣ ፋይናንስ እና ቱሪዝም ያሉ ዘርፎችን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል ግዙፍ አቅም መገንባቱን አረጋግጠዋል፡፡
በመጨረሻም ተቋማቱ የዲጂታል ኢትዮጵያ ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን ቋሚ የጋራ መድረክ በመፍጠር የዜጎችን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ላይ በቅርርብ ለመሥራት ወስነዋል፡፡
#RealizingDigitalEthiopia