ኢትዮ ቴሌኮም የእንስሳት አያያዝን የሚያዘምን እና የሚገኙበት ቦታ በቀላሉ ለማወቅ የሚያስችል ዲጂታል ላይቭስቶክ ትራኪንግ ሶሉሽን ተግባራዊ አደረገ!
ኩባንያችን በዛሬው ዕለት በላቀ አይ.ኦቲ (IoT) የተደገፈ እና የሀገራችን የእንሰሳት አስተዳደርን ለማዘመን የሚያስችል ክላውድን መሰረት ያደረገ ዲጂታል የእንሰሳት መከታተያ ሶሉሽን (Digital Cattle Tracking Solution) ተግባራዊ ማድረጉን በታላቅ ደስታ ይገልጻል።
ይህ ዘመናዊ ሶሉሽን አርሶ አደሮች እና እንሰሳት አርቢዎች በቀላሉ እንስሳቶቻቸውን መከታተል፣ ያሉበትን ቦታ መለየት እና የጤና ሁኔታቸውን መገምገም እንዲችሉ፣ ምርታማነትን ለማሳደግ በተለይም የእንስሳት ባለቤቶች የፋይናንስ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ የፋይናንስ ተደራሽነት ክፍተት ለማጥበብ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡
በተጨማሪም የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ገበሬዎችን እና ሌሎች እንስሳት አርቢዎችን ለማበረታታ፣ የእንስሳት እርባታ አያያዝን እና የግብርና ዘርፉን ለማዘመን በተለይም የእንስሳትን ዋጋ እና ጤንነትን መገምገም የፋይናንስ ተቋማትም የእንስሳትን ሀብት እንደ መያዣ በመቀበል አርብቶ አደሮችና አርሶ አደሮች የብድርና የኢንሹራንስ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡
ይህም ኢትዮጵያ ወደ ዘመናዊ እና ይበልጥ የቴክኖሎጂ ትስስር ወዳለው ግብርና በመግባት የዲጂታል ኢትዮጵያ ራዕይን እውን ለማድረግ የምታደርገውን ሁሉገብ ግስጋሴ የሚያጠናክር ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- https://bit.ly/43c67bG
#RealizingDigitalEthiopia #DigitalAfrica