ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ቃሊቲ የሚገኘውን የኮርፖሬሽኑን የኢንዱስትሪ መንደር ጎበኙ
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ( ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) ካነገበው ራእይ እና ተልእኮ አንጻር በአፍሪካ ምርጥ ሦስት የኮንስትራክሽን እና ማኑፋክቸሪንግ ኩባንያዎች መካከል አንዱ ለመሆን የሚያስችሉትን ተግባራት እያከናወነ መሆኑን መመልከታቸውን የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኮርፖሬሽኑ በቅርቡ የኮንስትራክሽን ግብአት ምርቶችን በስፋት እና በጥራት በማምረት ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ እንደሚያቀርብ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።
በጉብኝታቸው በኮርፖሬሽኑ እየተከናወኑ ያሉ የሪፎርም ተግባራት እና ያስገኙት ውጤት እውነትም የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጊዜ መጀመርን የሚያሳይ መሆኑን የጠቆሙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተመስገን ጥሩነህ የሥራ አካባቢን ጽዱ እና ምቹ ከማድረግ፣ የፕሮጀክቶች አፈጻጸምን ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ከማስተዳደር፣ የሰው ሀይልን ምርታማነት ከማሻሻል፣ የፕሮጀክቶች አፈጻጸምን ከማላቅ እና ትርፋማነትን ከማሳዳግ አንጻር የተከናወኑ ተግባራት ሌሎች ተቋማት ሊማሩበት የሚገባ ነው ብለዋል።
የኢ.ኮ.ሥ.ኮ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው የኮርፖሬሽኑን 'ከየት ወዴት' ለጎብኚዎች ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በቀጣይ የኮርፖሬሽኑን የልህቀት ትልሞች በመተግበር ረገድ የኮርፖሬሽኑ አመራሮች እና ሠራተኞች ለውጡን በላቀ ሁኔታ እንደሚያረገረጋግጡ አብራርተዋል።
በጉብኝቱ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና የኢ.ኮ.ሥ.ኮ አመራሮች ተገኝተዋል።