ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ እና በጀት በጥራት እንዲጠናቀቁ ተገቢ ክትትል መደረግ እንዳለበት ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ እና በጀት በጥራት እንዲጠናቀቁ ተገቢ ክትትል ማድረግ እንዳለበት አሳስቧል።
ቋሚ ኮሚቴው የሚንስቴር መስሪያ ቤቱን የ2017 ዓ.ም የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ገምግሟል።
የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር እሸቱ ተመስገን፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ እና በጀት በጥራት እንዲጠናቀቁ የጀመራቸውን ተግባራት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
በዘርፋ ጥራትን ለማስጠበቅ ቁጥጥር ማድረግና የህንጻ ደረጃዎችና ኮዶችን የሚመለከቱ መረጃዎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማደራጀት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል ።
የአረንጓዴ ልማት ስራዎችም ከሌሎች አገሮች ጋር ለመወዳደር በሚያስችል መልኩ ደረጃ ሊኖራቸው እና ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል ።
በተጨማሪም የኮሪደር ልማት ስራው ጥሩ መሆኑን ጠቁመው የመኪና ማቆሚያ፣ የመጫኛና ማውረጃ ቦታዎችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል ።
በዘርፉ ዲጂታላይዜሽን ማጠናከር፣ጥሩ ተሞክሮዎችን ማስፋት እና የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸዋል ።
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ ፣ በጀትና በጥራት እንዲጠናቀቁ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
የኮሪደርና የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ለከተሞችና ለነዋሪዎች ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳላቸው ገልፀዋል ።
ክብርት ሚንስትሯ ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎችን በሚመለከት በግማሽ ዓመቱ አጠቃላይ ሽፋን 175ሺ 879 ኪ.ሜ መሆኑን ገልጸዋል ።
የፕላን ዝግጅት ስራ በሚመለከት ከዚህ በፊት ፕላን ያልነበራቸው 16 አነስተኛ ከተሞችን ፕላን እንዲኖራቸው መደረጉን ገልጸዋል ።
የከተማ መሬትና ካዳስተር ስራዎች ጋር በተያያዘ በክልልና ከተማ አስተዳደሮች ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል 7ሺ ሄክታር መሬት ለማቅረብ ታቅዶ በምደባና በጫረታ ከ11ሺ ሄክታር በላይ መሬት ማቅረብ መቻሉን ገልጸዋል።
ያለፈቃድ የተያዙ ቦታዎችን በሚመለከት ወደ 85ሺ 256 ይዞታዎች ስርአት
እንዲይዙ መደረጉን ገልጸዋል ።
የቤቶች ልማትን በሚመለከት በግማሽ ዓመቱ 8ሺ ቤቶች ለመገንባት ታቅዶ ወደ 20ሺ 754 ቤቶች መገንባታቸውን ገልጸዋል።
በዘርፉ ከ110ሺ በላይ ቋሚ እና ጊዜያዊ የሥራ እድል መፈጠሩን እና ሌሎች በግማሽ ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር አቅርበዋል።
(ፖርላማ)