🔷መቃብር View Apartment☠💀
ሰሞኑን በአንድ ስራ የሄድኩበት አካባቢ ያለ ሰፊ የመቃብር ቦታንና የእምነት ተቋም አጎራብቶ የተገነባ የሪል እስቴት ፕሮጀክት ተመለከትኩ። የሚገርመው አብዛኛው የመኝታ ቤቶቻቸው መስኮቶቻቸው ወደ መቃብር ስፍራው ሆነው የተገነቡት ቤቶች በርካታ ናቸው።
ከእኛ ማህበረሰብ ስነልቦና አንጻር መቃብር ቦታን እናከብራለን እንፈራለንም ። የእምነት ተቋማት አጎራባች ሆኖ የመኖር ጉዳይ እንደ አማኙ ምቾትና ምርጫ ቢለያይም ከመቃብር ቦታ መጎራበት ግን ብዙም ምቾት የሚሰጥና የሚመረጥም አይደለም።
እንደዚህ አይነት ቤቶች ለአልሚዎችም ቢሆን ጥሩና አዋጭ ይሆናል ተብሎ አይጠበቅም ምክንያቱም የቤቶቹ ተፈላጊነት በአንድም በሁለትም ምክንያት ይቀንሳል።ፈላጊው ሲቀንስ ፕሮጀክቱ የተወሳሰበ ችግር ውስጥ ገብቶ መጨረሻው ኪሳራ ሊሆን ይችላል። የመሸጫ ጊዜው ይረዝማል በመርዘሙም ተፈላጊነቱ እየቀነሰ ይሄዳል፣ የመሸጫ ዋጋው ይወርዳል፣ ብድር ካለበት ለተጨማሪ ወለድ ክፍያ ይዳረጋል...ለቢዝነስ፣ ወለድ፣ገበያ ፣ ሊኩዲቲ የመሳሰሉ የ Real Estate Investment Risk ተጋላጭ ይሆናል ይከስራል።
የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት ጥቅሙ ከፍ ያለ ነው እንደሚባለው ሁሉ ኪሳራውም ይዞ የሚጠፋ እጅግ አስከፊ ነውና ኢንቨስትመንት ውስጥ የሚገቡ ሰዎች የMarket & Marketability ጥናት ቢያሰሩ በጥናቶቹ ውስጥም የቤት ገዢ ታሳቢ ደንበኞች ( Target Customers) ባህልና ንዑስ-ባህልን አብሮ እንዲጠናን ቢያደርጉ ከሚመጣባቸው ያልታሰበ ቁጣ ይድናሉ።
በአንጻሩ ጥሩ ጸጥታን ለሚሹ፣ መቃብር ስፍራን እንደ አረንጓዴ ስፍራ ለሚቆጥሩ ሁኔታው ለማያውካቸው ጥቂቶች ቆራጦች በጥሩ ዋጋ ቤት ማግኘት ለሚሹም ጥሩ አማራጭ ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን መልሶ የመሸጥ አላማ ላላቸው ተመካሪ አይደለም።
ለማንኛውም ባየሁት ፕሮጀክት ላይ በመቃብሩ በኩል ቤት የገዙ የሪል እስቴቱ ደንበኞች ከወዲሁ የማይክል ጃክሰንን Thriller ክሊፕ እያዩ ራሳቸውን በእውንም በህልምም ከሁኔታው ጋር እንዲያለማምዱ ይመከራሉ።
የሪል እስቴት አገበያዮች "መቃብር ቪው " ብለው ይሸጡልናል ወይስ "ግሪን ቪው"? ለዚህ አይነት ግብይት ስንት ፐርሰንት ኮሚሽን ይጠይቁ ይሆን?
በሪል እስቴት ግብይት ውስጥ እንዲህ ያሉ ንብረቶች Stigmatized Properties ይባላሉ ለማገበያየት ጊዜ ስለሚወስዱና ፈላጊያቸው ጥቂት በመሆኑ የሚከፈልባቸው የሽያጭ ኮሚሽን ከፍ እንዲል ይመከራል።
(በኢንጂነር ደሳለኝ ከበደ)