ከአዲስ አበባ የሚወጡ 4 የፍጥነት መንገዶች ለመገንባት ጥናት እየተደረገ ይገኛል
ከአዲስ አበባ በተለያዩ መስመሮች የሚወጡ 4 አዳዲስ የፍጥነት መንገዶችን ለመገንባት የሚያስችል ጥናት እየተደረገ ይገኛል፡፡
ጥናቱ እየተደረገ የሚገኘው ከአዲስ አበባ ደሴ ፣ከአዲስ አበባ ጅማ ፣ከአዲስ አበባ ደብረማርቆስ እና ከአዲስ አበባ ነቀምት በሚዘልቁት መንገዶች ላይ ነው፡፡
እነዚህ የፍጥነት መንገዶች የሚገነቡበት የጥራት ደረጃ ፣ የሚኖራቸውም አጠቃላይ የጎን ስፋት ከፍ ያለ እና የሚገነቡበት መልክአ ምድር አብዛኛውን ተራራማ ቦታዎችን የሚሸፍን በመሆኑ ከፍተኛ የሆነ ወጪ እና የቆረጣ ስራዎችን የሚጠይቁ ናቸው፡፡
በጥናቱ መሰረት ፕሮጀክቶቹ የሚኖራቸው ርዝመት በአማካይ 300 ኪሜ ሲሆን ግንባታቸውም በተለያዩ ምዕራፎች እና በተወሰነ ኪሎሜትር ተከፋፍሎ የሚጀመር ይሆናል፡፡
በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቶቹ የአዋጭነት፥ እንዲሁም መሰረታዊ የዲዛይንና የዝግጅት ሥራ እየተከናወነ ሲሆን ለዝግጅት ሥራው የሚያስፈልጉ የጥናት ስራዎችንም ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው።
አራቱን የፍጥነት መንገዶች ለመገንባት የሚያስፈልገው ወጪ የሚሸፈነው በመንግስትና የግል አጋርነት ትብብር ነው፡፡
ከፍጥነት መንገዶቹ መካከል የአዲስ ጅማ እና አዲስ ደብረ ማርቆስ ፕሮጀክቶች ለገንዘብ ሚኒስቴር የመንግስት የግል አጋርነት ቦርድ የቀረቡ ሲሆን ቀሪዎቹም በቅርቡ ይቀርባሉ ተብለው ይጠበቃል ።
ፕሮጀክቶቹም በገንዘብ ሚኒስቴር የመንግስት የግል አጋርነት ትብብር ቦርድ ከጸደቁ በኋላ ወደ ቀጣይ ስራ ይገባሉ።
(ኢመአ)