በሰርጀሪ ገጽታውን መሉ በሙሉ ያስቀየረው ግለሰብ
አንድ ግለሰብ በፕላስቲክ ሰርጀሪ የተሸበሸበው ቆዳው የወጣት መልክ፣ የተመለጠው ፀጉሩ ሙሉ፣ አፍንጫው ሰልካካ፣ አጠቃላይ አካላዊ ገጽታውም ከዋናው እድሜው ቢያንስ ከሁለት አስርት ዓመታት በታች ሆኗል ቢባል የማይታመን የቁም ቅዠት ሊመስል ይችላል፡፡ ይህ ግን እውነት ሆኗል።
በቱርክዬ ኢስታንቡል ከተማ የሚገኘው የፕላስቲክ ሰርጀሪ (ቀዶ ጥገና) ክሊኒክ አንድን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ግለሰብ ከሰርጀሪው በፊት እና በኋላ የሚያሳዩ ፎቶዎችን በማንሳት የለቀቀው ፎቶ አነጋጋሪ ሆኗል።
ከሰርጀሪው በፊት እና በኋላ ያለውን ለውጥ የሚያሳይ ፎቶ ጎን ለጎን ተደርጎ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተለቋል። ለውጡ እጅግ በጣም አስገራሚ የሆነ፣ ፈጽሞ ሊታሰብ እና ሊታመን የማይችል በመሆኑም በማኅበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ ትኩረት ስቧል።
ይህ ከሰሞኑ የበይነ መረብ ሚዲያውን ያጨናነቀው ፎቶ እስቴ ሜድ የተሰኘው ክሊኒክ ባለፈው ሳምንት ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው ታካሚ ላይ የሰራው አስደናቂ ስራ ነው።
ከህክምናው በኋላ ያለውን የግለሰቡን መልክ የሚያሳየው ፎቶ ሰውዬው ከዋናው እድሜው ቢያንስ ከሁለት አስርት ዓመታት በታች የሆነ ከማስመሰሉም በላይ በወጣትነቱ የሌለውን መልክ አላብሶታል።
ሁለቱ ፎቶዎች እጅግ የተራራቁ በመሆናቸው አንድ ላይ ባይለጠፉ ኖሮ አብዛኛው ሰው አንድ ሰው ነው ብሎ ሊገምት የሚችልበት ምንም አይነት ምስስሎሽ አይታይም።
በሚካኤል ፎቶ ላይ አስተያቱን የሰጠ አንድ የኢንስታግራም ተጠቃሚ “የጣት አሻራ ማረጋገጥ አለብን ይህ የማይታመን ነው። ቱርክዬ ውስጥ ምን ዓይነት ተዓምር እየሰሩ ነው?" ሲል ግርምቱን አስቀምጧል። ሌሎችም እንዲሁም አግራሞታቸውን ገልጸዋል።
ሰለ አስትሮኖሚ ብቻ የሚወራበተን ቻናል ለመቀላቀል
@ethio_tefer0 @ethio_tefer0
🚀Join