ያልተጌጠበት ወርቅ
ምድሯ ማዕድናት የመሉባት፣ ሃብት የበዛላት ፣ ያልተነካ ጸጋ የሚገኝባት ናት፡፡
በሁሉም አካባቢዎች አጀብ የሚያሰኙ ጸጋዎች በዝተውላታል፡፡
የተከማቹት ሃብቶች ሀገርን የሚያሳድጉ፣ ሕዝብን በሃብት ማማ ላይ የሚያቆናጥጡ ናቸው፡፡ ነገር ግን ለዘመናት ተቀብረው የተጠቀመባቸው፣ አውጥቶ ያጌጤባቸው፣ ፈልፍሎ የከበረባቸው አልነበሩም፡፡
ከወርቅ ላይ ተኝተው የማያጌጡት፣ ከሕብስት ላይ እየኖሩ የሚራቡት፣ ከሥራ ላይ ተቀምጠው ሥራ አጥ የኾኑት ብዙዎች ናቸው፡፡ የሚታዩት እና የማይታዩት፣ የሚዳሰሱትና የማይዳሰሱት ሃብቶች መገኛ ናት፡፡ በየብስም ቢሉ በባሕር፣ በሜዳ ቢሉ በተራራ ተፈጥሮ ያደላት፣ ታሪክ ያከበራት፣ ጸጋ የበዛላትእና የበዛባት ሀገር ናት ኢትዮጵያ፡፡
ኢትዮጵያ የማዕድናት ሃብታም እንደኾነች ይነገርላታል፡፡ በምድሯ አያሌ ማዕድናት እንዳሉ ይነገራል፡፡ ነገር ግን በምድሯ የተከማቹትን ሃብቶቿን አልተጠቀመችባቸውም፤ ለዘመናት ቀብራ አስቀምጣቸው ኖረች እንጂ፡፡ ሃብቶቿን ሳትጠቀም ለዓመታት ከውጭ የማዕድን ምርቶችን ስትገዛ ኖራለች፡፡
አንዳንድ የስ ምድር ባለሙያዎች ኢትዮጵያ በማዕድን ላይ የተሠራች ሀገር ናት ትባላለች ይላሉ፡፡ ለዚህም ማሳያቸው የማዕድኗን ውበት እና ብዛት ስላዩ ነው፡፡
የማዕድን ሃብት በስፋት ከሚገኝባቸው አካባቢዎች ደግሞ የአማራ ክልል አንደኛው ነው፡፡ በክልሉ አዲስ ተስፋን የሚሰጥ በርካታ የማዕድን ክምችት እንዳለ የክልሉ የማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ ይገልጻል፡፡
በክልሉ ያለው የማዕድን ክምችት የበርካታ ወገኖችን ሕይወት የቀየረ፣ ለክልሉም ተስፋን እየሰጠ ይገኛል፡፡
ማዕድን የሚያወጡ፣ የሚወጣውን ማዕድን ተቀብለው እሴት የሚጨምሩ፣ ወደ ገበያ የሚያቀርቡት ወይም ወደ ውጭ ገበያ የሚልኩት የሥራ እድል ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ ወደፊት የሀገራችን ኢኮኖሚ ብሎም በስፋት የሥራ እድል ይፈጥራሉ ተብለው ተስፋ ከሚጣልባቸው ዘርፎች መካከልም ማዕድን አንዱ ነው ተብሏል፡፡
የአበክመ የማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ ደግሞ ክልሉ በማዕድን ሃብት የበለጸገ መኾኑን በጥናት እያረጋገጠ ይገኛል፡፡ በየጊዜው በርካታ የማዕድን ክምችት እንደሚገኝም በክልሉ እንደሚገኙ በጥናት ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
ማዕድን የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት እና የክልሉን ምጣኔ ሃብት ከፍ በማድረግ የራሱ አስተዋጽዖ አለው።