የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ.መ.ቁ 211028 ጥር 27 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ አለመስጠት ጋር በተገናኘ የአንድ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ በወንጀል ተጠያቂ የሚሆነው እሱ የሚመራው ድርጅት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆኖ ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ ግብይት ማከናወኑ ሲረጋገጥ እንደሆነ: የድርጅቱ ሀላፊነት ከተረጋገጠ የስራ አስኪያጁ ሀላፊነት የሕግ ግምት የሚወሰድበት ስለመሆኑ: ሆኖም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ የድርጅቱን አስተዳደር በሚመለከት በውክልና ለሌላ ሰው ያስተላለፈ መሆኑ እና ተወካዩም በተቀበለው ውክልና መሠረት ሥራውን የሚያከናውን መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ ተጠያቂ የሚሆነው ውክልናውን ተቀብሎ ሥራውን በውክልና የሚያስተዳድረው ሰው እንጂ ስራ አስኪያጁ ወይም የድርጅቱ ባለቤት ሊሆን አይገባም በማለት ወስኗል።
Credit- Etmet Assefa (Consultant and attorney at Law Former Judge at federal supreme court of Ethiopia )